አርሜተር የተባለው የወባ መድሃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል ታገደ

ቅዳሜ መስከረም 18 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ” አርቲሜተር ” የተባለውን በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል አግጃለው ብሏል፡፡

ባለስልጣኑ አደረኩት ባለው የገበያ ቅኝት መድኃኒቱ መገኘቱን ፣ በባለስልጣኑ ያልተመዘገበ እንዲሁም ናሙናው ተወስዶ በላብራቶሪ ሲፈተሽ አርቲሜተር የተባለው ንጥረ ነገር በውስጡ አለመገኘቱ መረጋገጡን ገልጿል፡፡

በዚህም ይህን መድኃኒት የጤና ባለሙያዎች እንዳይጠቀሙት እና በየደረጃው ያሉ የክልል ተቆጣጣሪዎች በየአካባቢያቸው ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርምጃዎች እንዲወስዱ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡

መድኃኒቱ ‘ ሻይንፋርም ‘ በተባለ የቻይና የመድሃኒት አምራች የተመረተ ሲሆን፤ አርቲሜተር የሚል ስያሜ ያለው እና በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ነው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here