ማክሰኞ መስከረም 20 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ የምስጋና በዓል የሆነው ኢሬቻ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት እንዲመዘገብ እየተሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡
የኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ጀሚላ ሲምቢሩ የኢሬቻ በዓል የወንድማምችነት፣የአንድነት በዓል በመሆኑን ለዓለም ህዝብ ለማስተዋወቅ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
በኢሬቻ በዓል የሚታደሙ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የገለጹት ኃላፊዋ፤ ይህም በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
የኢሬቻ በዓል ቱውፊቶችን እና ባሕላዊ ክንውኖችን ለማስተዋወቅ ባለ ድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የኢሬቻ በዓል መስከረም 25 እና 26 ይከበራል፡፡



