“የኢሬቻ በዓል በዩኔስኮ በቅርስነት እንዲመዘገብ እየተሰራ ነው” የኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ

0
283

ማክሰኞ መስከረም 20 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ የምስጋና በዓል የሆነው ኢሬቻ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት እንዲመዘገብ እየተሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡

የኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ጀሚላ ሲምቢሩ የኢሬቻ በዓል የወንድማምችነት፣የአንድነት በዓል በመሆኑን ለዓለም ህዝብ ለማስተዋወቅ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

በኢሬቻ በዓል የሚታደሙ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የገለጹት ኃላፊዋ፤ ይህም በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

የኢሬቻ በዓል ቱውፊቶችን እና ባሕላዊ ክንውኖችን ለማስተዋወቅ ባለ ድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢሬቻ በዓል መስከረም 25 እና 26 ይከበራል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here