የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአምስት ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች የስራ ፈቃድ ሰጠ

0
296

ዕረቡ መስከረም 22 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ አገልግሎት እና ተደራሽነት ለማስፋት ከባንክ ጋር ከተያያዙ የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች በተጨማሪ ከባንክ ጋር ዝምድና የሌላቸው የግል የውጪ ምንዛሬ ቢሮዎችን ለመክፈት የሚያስችል የውጭ ምንዛሬ መመሪያ አውጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት አምስት የግል የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች ተፈላጊውን መስፈርት በማሟላታቸው የስራ ፍቃድ እንደተሰጣቸው ባንኩ ገልጻል፡፡

እነሱም ዱግዳ ፊደሊቲ ኢንቨስትመንት፣ ኢትዮ ኢንዲፔንደንት፣ ግሎባል፣ ሮቡስት እና ዮጋ ፎርኤክስ የተባሉ የግል የውጪ ምንዛሬ ቢሮዎች ናቸው፡፡

በመሆኑም ቢሮዎቹ ሙሉ ተቀባይነት ያላቸው እና የውጭ ሀገር ጥሬ ገንዘቦችን በመግዛት እና በመሸጥ እንዲሁም ከባንኮች ጋር በመቀናጀት ለወጪ እና ገቢ ንግድ የሚውል የውጭ ምንዛሬ በማመቻቸት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል፡፡

እንዲሁም በዋናነት የሚያካሂዱት የውጭምንዛሪ ሽያጭም ሆነ ግዢ ወዲያውኑ የሚፈጸም ብቻ ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ቢሮዎቹ ያለ ጉምሩክ ማረጋገጫ ከደንበኞች እስከ 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር፣ የጉምሩክ ፈቃድ ለሚያቀርቡ ደግሞ ከዚያ በላይ የውጭ ምንዛሬ በጥሬ ገንዘብ መግዛት የሚችሉ ሲሆን ተፈላጊ የጉዞ መረጃ ላላቸው የግል ተጓዞች እስከ 5 ሺህ የአሜሪካን ዶላር እና ለንግድ ተጓዞች ደግሞ እስከ 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በጥሬ ገንዘብ መሸጥ እንደሚችሉ ብሄራዊ ባንክ አስታውቋል፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here