ከቆቃ ወደ ሁርሶ በተዘረጋ በባለ 230 ኪሎ ቮልት ጥምር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር መሰረቁ ተገለጸ

0
331

ሐሙስ መስከረም 23 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከቆቃ ወደ ሁርሶ በተዘረጋ በባለ 230 ኪሎ ቮልት ጥምር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተፈጸመ ሥርቆት በምሥራቅ ኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች ኃይል መቋረጡን አስታውቋል።

ስርቆቱ የተፈጸመው በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ አዋሽ ፓርክ አካባቢ ሲሆን መስመሩ ለአዲስ አበባ-ጅቡቲ የባቡር መስመር እንዲኹም ለጎረቤት ጅቡቲ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚያቀርብ መሆኑ ተገልጻል፡፡

በሥርቆቱ ምክንያት ከወደቀው አንድ ምሰሶ በተጨማሪ ሌሎች ሰባት የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎችም በአስጊ ሁኔታ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡

የጥገና ጊዜውም እስከ 20 ቀን እንደሚፈጅ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡

የጥገና ሥራው ሙሉ በሙሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስም ከመስመሩ ኃይል ሲያገኙ ለነበሩ ከተሞችና አካባቢዎች በፈረቃ ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ለማድረግ ጥረቶች ይደረጋሉ ተብሏል፡፡

በተጨማሪ አዋሽ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የባቡር መስመር ላይ በሚገኙ ዘጠኝ የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ ጉዳት በመድረሱ የጥገና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here