በሀገሪቱ የተከሰተው መሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ ሊከስት ይችላል ተባለ

0
336

እሁድ መስከረም 26 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በሀገሪቱ የተከሰተው መሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ ሊከስት ይችላል ሲሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጂዮፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር  ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር) በተለይም አዲስ አበባ ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ የመከሰት እድሉ ሰፊ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ስምጥ ሸለቆና የስምጥ ሸለቆ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ነቅተን የምንጠብቀው ነገር መሆን አለበት ብለዋል።

ለጊዜው መናገር የምችለው ከበድ ያለ ነገር አይመጣም ብለን ነው የምንገምተው ነገር ግን ከበድ ያለ ነገር ከመጣ:-

– የቤት ቋሚዎች በተለይ ኮንዶሚኒየም ህንጻ ላይ ያሉ ሰዎች ኮለኖች አካባቢ መጠጋት

– ከተቻለ ጠረጴዛ ስር መግባት

– ሊፍት አለመጠቀሙ

– ውጪ ላይ የመብራትና መሰል ምሶሶዎችን አለመጠጋት ያስፈልጋል ሲሉ ዳይሬክተሩ መክረዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here