በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች  የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር ነዋሪዎች ገለጹ

0
290

እሁድ መስከረም 26 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች  የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር ነዋሪዎች ገለጸዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ምሽት 2:15 ላይ በተለይ በኮዬ ፈጬ ፣ ሰሚት ፣ የካ አባዶ ፣ ሃያት ፣ ሲኢሚሲ እና ቦሌ አራብሳ መጠነኛ የመሬት ንዝረት እንደነበር ነዋሪዎች ገልፀዋል።

በተለይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች በስጋት ወደ መሬት ወርደው እንደሚገኙ አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

የመሬት መንቀጥቀጡ በአዳማ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ ነዋሪዎች ከተቀመጡበት እስከመጣል የደረስ ንዝረት እንደነበር የአዲስ ማለዳ ባልደረባ በስፍራው ተመልክቷል።

በሌላ በኩል ከአዳማ ከተማ ቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው መተሃራ ከተማ ላይ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አዲስ ማለዳ ከምንጮቿ ሰምታለች።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here