የዳሸን ባንክ አጠቃላይ ሃብት 183.7 ቢሊየን ብር መደረሱ ተገለጸ

0
291

ማክሰኞ ጥቅምት 05 ቀን 2016(አዲስ ማለዳ) የዳሸን ባንክ አጠቃላይ ሃብት ባለፈው በጀት ዓመት የ27 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ ብር 183.7 ቢሊየን መደረሱን ገልፀዋል፡፡
ባንኩ ባለአክሲዮኖች 31ኛ መደበኛና 26ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በዛሬው እለት በሚሊንየም አዳራሽ ያካሄደ ሲሆን ያለፈው ዓመት የባንኩ የስራ አፈፃፀም፣ የዚህ በጀት ዓመት እቅድና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከባለአክሲዮች ጋር ተወያይቷል፡፡

በበጀት ዓመቱ የዳሸን ባንክ ተቀማጭ የገንዘብ መጠን የ30.9 ቢሊየን ብር እድገት ማስመዝገቡንና የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን 145.9 ቢሊየን ብር መድረሱን የዳሸን ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ዱላ መኮንን ተናግረዋል፡፡

ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ለባንኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ያበረክተው ድርሻ 11.1 ቢሊየን ብር እንደነበርም ጠቁመዋል፡፡

የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በበኩላቸው ያለፈው ዓመት ምንም እንኳን የተለያዩ ተግዳሮቶች ቢኖሩም ባንኩ ይህን ተቋቁሞ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ጠቁመዋል፡፡

የዳሸን ባንክ አጠቃላይ ሃብት ባለፈው በጀት ዓመት የ27 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ ብር 183.7 ቢሊየን መደረሱን ገልፀዋል፡፡

ባንኩ ባለፈው በጀት ዓመት 1.44 ሚሊየን አዳዲስ ደንበኞችን ማግኘት እንደቻለና ይህም ለባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ዕድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከቱንም ገልፀዋል፡፡

ባንኩ በአሁኑ ወቅትም ከ6.7 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉት የተመላከተ ሲሆንባለፈው በጀት ዓመትም ከ6.4 ቢሊየን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here