ባንኮች የውጭ ምንዛሬን የሚገዙበትና የሚሸጡበት የልዩነት መጠን ከ2 በመቶ እንዳይበልጥ የሚገድብ መመሪያ ይፋ ሆነ፡፡

ማክሰኞ ጥቅምት 05 ቀን 2016(አዲስ ማለዳ)ብሄራዊ ባንክ አዲስ ያወጣው መመሪያ ባንኮች በየቀኑ በሚያወጡት የውጭ ምንዛሬ የመሸጫና የመግዣ መጠን ላይ ልዩነቱ ከሁለት በመቶ በላይ እንዳይሆን የሚገድብ እንደሆነም አስታውቋል፡፡

ከውጭ ምንዛሬ ተመን ጋር በተገናኘ ተያያዥ አሰራሮችን በመውሰድ የውጭ ምንዛሬ የመግዣና መሸጫ ልዩነት በአለም አቀፍ አሰራሮች እንዲቃኙ ማስፈለጉን ያስታወቀው ባንኩ የተደረገው የፖሊሲ ማሻሺያ የባንኮች ገቢያ መር የውጭ ምንዛሬ አሰራር የሚጋፋ እንዳልሆነመም እወቁልኝ ብሏል፡፡

በሌላ በኩል በአዲሱ የፖሊሲ ማሻሺያ ባንኮች ስለሚሰጡት የውጭ ምንዛሬ አገልግሎት ለደንበኛቻቸውም ሆነ ለሚመለከተው ተቆጣጣሪ አካል ማሳወቅና ተያያዥ ሪፖርቶችን ማቅረብ እንደሚገባ ተቀምጧል፡፡

እንደ ብሄራዊ ባንክ መረጃ በአጠቃላይ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ የአገልግሎት አሰጣጥን ከአለም አቀፍ ተሞክሮዎችና ልምዶች ጋር አጣጥመው መጓዝ ስላለባቸው ይህ የፖሊሲ ማሻሺያ እንዲደረግ አስገድዷል ፡፡

የኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ ሃምሌ 22 2016 ዓ.ም ገቢያ መር የውጭ ምንዛሬ አሰራርን ማጽደቁ የሚታወስ ነው፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here