የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር አድርጎት የነበረውን ስምምነት በሚመለከት አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ

0
373

ረቡዕ ጥቅምት 06 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2018 ከፌዴራል መንግስቱ ጋር የተፈራረመውን የሰላም ስምምነት አፈጻጸም በሚመለከት ውይይት ለማድረግ ልዩ ስብሰባ ጠርቷል፡፡

ነጻ አውጪ ግንባሩ የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ከፈረንጆቹ ጥቅምት 25-27 እንደሚያከናውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በስበሰባው በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለመወያየትና ግንባሩ ከዚሁ ጋር በተያያዘ መውሰድ ስላለበት አቋም በዝርዝር ለመወያየት ማቀዱም ታውቋል፡፡

የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ከቅርብ ጊዚያት ወዲህም ከፌዴራል መንግስቱ ጋር ያሰርኩት ስምምነት በተገቢው መንገድ እየተተገበረ አይደለም ሲል ተደጋጋሚ ወቀሳዎችን ሲያቀርብ ይደመጣል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here