የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ

ሐሙስ ጥቅምት 14 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች አማራጭ ድረ-ገጾችን ተጠቅመው ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በ2016 የ12ኛ ክፍል ማጠቃሊያ ፈተናን ከወሰዱ ተፈታኞች መካከል ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግባት የቻሉት 5.4 በመቶ ብቻ መሆናቸው መገለጹ የሚታወስ ነው፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here