እሁድ ታሕሳስ 6፣ ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የኦሮሚያ ክልል ሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ በነገው ዕለት በአዳማ ከተማ ይጀምራል።
በመድረኩ ከክልሉ 356 ወረዳዎች የተመረጡ ከ7 ሺህ 500 በላይ የህብረተሰብ ወኪሎች በ4 የተለያዩ ቡድኖች ተከፍለው የሚመክሩ መሆኑን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር መሐሙድ ድሪር ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
አዲስ ማለዳ ኮሚሽኑ ከነገ ሰኞ ታሕሳስ 7/2017 ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማ የሚያካሄደውን የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍን በሚመለከት በስፍራው ተገኝታ መረጃዎችን ወደ እናንተ የምታደርስ ይሆናል።



