መቀሌ ከተማ በሁለቱ የህወሓት ቡድኖች የተመደቡ ከንቲባዎች በስራ ገበታ ላይ የሉም ተባለ

0
195

ታኅሳስ 09 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በሁለቱ የህወሓት ቡድኖች የተመደቡ ከንቲባዎች በስራ ገበታ ላይ የሌሉ ሲሆን የከንቲባ ፅህፈት ቤት ታሽጎ በፀጥታ ሃይሎች ጥበቃ ስር እንደሚገኝ ተገልጋዮች መናገራቸው ተገልጿል።

በአስተዳደሩ ዋና በር በቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ተገለግጋዮች ሲገቡ ሲወጡ ይታያሉ ፤ ፍትሻ በሚካሄድበት ቦታ ከተለመደው በተለየ ብዛት ያላቸው የፀጥታ አካላት እንደሚስተዋሉ ተመላክቷል።

ከከንቲባ የሚሰጥ አገልግሎት ለማግኘት ከአንድ ወር በላይ እየተመላለሱ ያሉ ተገልጋዮች እስካሁን ምንም አይነት አገልግሎት አለማግኘታቸውን እና በመጉላላት ላይ መሆናቸውን ቲክቫህ ዘግቧል፡፡

” በሁለቱም በኩል ያሉ የህወሓት አመራሮች ማሰብ ተሰኗቸዋል ፤ ህዝቡ ከገባበት የጦርነት ጦስ እንዲያንሰራራ ከመምራት ይልቅ ለስልጣናቸው ብቻ ሲሯሯጡ የህዝቡን ስቃይ እጅግ መራራ አድርገውታል ” ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

ባለፈው ወርሃ ጥቅምት 2017 ዓ.ም የቀድሞ ከንቲባ ይትባረክ ኣምሃ ተክቶ በደረብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት እጩ አቅራቢነት በከተማው ምክር ቤት ከንቲባ ሆነው የተሾሙት ረዳአ በርሀ (ዶ/ር) በጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ወድያውኑ ተቀባይነት ማጣታቸው ተከትሎ ታህሳስ 23ቀን2017 ዓ.ም ብርሃነ ገ/የሱስ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ተሹመዋል።

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ምክር ቤቶች በመጠቀም ፤ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት ደግሞ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ” በተሰጠኝ ስልጣን መሰረት ” በማለት መቀሌን ጨምሮ በትግራይ ስድስት ዞኖች የየራሳቸው አስተዳዳሪዎች በመሾም ህዝቡን ግራ እያጋቡት መሆኑ ተጠቁሟል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here