የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የትምህርት ዘመን የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ።
በዚህም መሠረት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 24 እስከ ግንቦት 27/2012 እንደሚሰጥ የገለጸ ሲሆን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ደግሞ ከሰኔ 01 እስከ ሰኔ 03/2012 ድረስ እንደሚሰጥ ኤጀንሲው አስታወቋል።
ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሰዓት ይሰጡ የነበሩ የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተናዎች የተለያየ የማጠናቀቂያ ጊዜ የነበራቸው በመሆኑ በፈተናዎች አፈጻጸም ላይ ችግር ሲፈጠር መቆየቱን ኤጀንሲው ጠቁሟል።
ተመሳሳይ ሰዓት ያላቸውን ፈተናዎች ኬሚስትሪ እና ኢኮኖሚክስ፤ ባዮሎጂ እና ታሪክ በተመሳሳይ ሰዓት እንዲሰጡ ለውጥ መደረጉንም ኤጀንሲው ገልጿል።



