የአንጋፋው የማስታወቂያ ባለሙያ ውብሸት ወርቃለማሁ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ ረቡዕ የካቲት 25/2012 በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ተፈፀመ።
የቀብር ስነ ስርዓታቸውም ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመድ፣ የስራ አጋሮቻቸው እና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት ተፈፅሟል
ወብሸት ባደረባቸው ህመም በቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ባሳለፍነው ቅዳሜ የካቲት 21/2012 ነበር።
በኢትዮጵያ የማስታወቂያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ፈር ቀዳጅ የነበሩት ውብሸት፥ በሃገር ፍቅር ቴአትር ቤት ቴአትሮችን እንዲሁም የቴሌቪዥን ድራማዎችን በመፃፍ እና በመተወን እና አንበሳ የተባለ የማስታወቂያ ድርጅት በመክፈት በዘርፉ ሲሰሩ መቆታቸውም ይታወሳል።
ምስል ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት



