ዳሰሳ ዘ ማለዳ (የካቲት25/2012)

0
778

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የመንገደኞች ቁጥር 20 በመቶ እንደቀነሰበት ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወልደገብረማርያም የአየር መንገዱ መንገደኞች በ20 በመቶ መቀነሳቸውን ለሮተርስ ገለጹ።

በኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት ተጓዦች ከጉዞ ይልቅ ቤታቸው መቆየትን በመምረጣቸው የመንገደኞቹ ቁጥር ሊቀንስ  እንደቻለም አስታውቀዋል።

በዚህ ቫይረስ ሳቢያም የአፍሪካ አየር መንገዶችን 40 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማሳጣቱም ተገልጿል።(ኢትዮኤፍኤም)

……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የአንጋፋው የማስታወቂያ ባለሙያ ውብሸት ወርቃለማሁ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ ረቡዕ የካቲት 25/2012 በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ተፈፀመ። የቀብር ስነ ስርዓታቸውም  ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመድ፣ የስራ አጋሮቻቸው እና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት ተፈፅሟል።ወብሸት ባደረባቸው ህመም በቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት  ባሳለፍነው ቅዳሜ የካቲት 21/2012 ነበር።(አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በከተማዋ ከ13 ሺ በላይ ግብር ከፋዮች ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ ውዝፍ ዕዳ እንዳለባቸው አስታወቀ። በቢሮው የእቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር ጥላሁን ግርማ እንደገለጹት፤ ባለፉት ሰባት ወራት 4ሺ940 ግብር ከፋዮች 778 ሚሊዮን 295 ሺ 900 ብር ያለባቸውን ውዝፍ ዕዳ ሲከፍሉ በአንጻሩ 13ሺ 45 ግብር ከፋዮች ያለባቸውን አምስት ቢሊዮን 067ሚሊዮን 358 ሺ 343 ብር ውዝፍ ዕዳ አልከፈሉም ብለዋል።(የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኤሌክትሮኒክስ ክፍያን ለመተግበር ከሳፕ የሶፍት ዌር ኮርፖሬሽን ጋር እንደሚሰራ አስታወቀ። ሳፕ የተሰኘው አለም አቀፍ የሶፍትዌር ኮርፖሬሽን የአይቲ ሶፍትዌር አገልግሎቶችና በዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር ሊሰራ መሆኑን አስታውቋል። የጀርመኑ ኩባንያ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በሚፈጽመው ስምምነት ኩባንያው በቀላል የሃይል ቁጥጥር ስራ ፣በዘመናዊ የገቢ አሰባሰብ እና ክፍያ ስራዎች ላይ እንደሚሰማራ ተነግሯል።(ኢዜአ)

……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የኢትዮጵያ የንግድ ዉድድር እና ሸማቾች ባለስልጣን ህብረተሰቡ እንዳይመገባቸው ያላቸውን ዘጠኝ የታሸጉ የአሳ ምርቶችን ይፋ አደረገ።በቆርቆሮ የታሸጉ የአሳ ምርቶች በደቡብ አፍሪካ ደረጃ ተቆጣጣሪ መስሪያ ቤት በኩል በተደረገላቸዉ ፍተሸ የአስተሸሻገ ችግር ስለታየባቸዉ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸዉ ሲል አሳስቧል። የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ አገራት የጋራ ገበያ የንግድ ዉድድር ኮሚሽን/ ኮሜሳ የኢትዮጵያ የንግድ ዉድድር እና ሸማቾች ባለስልጣን መረጃዉን እንደላከ የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር  አላቃድር ኢብራሂም ምርቶቹ እ.ኤ.አ በ2019 የተመረቱና በታሸጉበት ቆረቆሮ አናት ላይ ZST29 እና ZSC29 የሚል ፅሁፍ አለባቸዉ ብሏል።(ኢትዮኤፍኤም)

……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ኅብረተሰቡ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ፕሬዝዳንቷ ሦስተኛውን ዙር የ8100 A የሕዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ዛሬ የካቲት 25/2012 በይፋ አስጀምረዋል፡፡አዲስ ይፋ የተደረገው የ8100 A የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ሽልማት ያለው እና ለስድስት ወራት የሚቆይ መሆኑም ታውቋል። ከዚሁ ጎን ለጎን የግድቡን ግንባታ ለማገዝ የሚያስችሉ ሌሎች የገቢ ማሰባሰቢያ መድረኮች እንደሚዘጋጁም ተነግሯል።(ኢቢሲ)

……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም የሆነው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ስምንት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች ከእስር የተፈቱ ሲሆን የቀድመው የኦነግ የቀድሞ ጦር አዛዥ የነበሩት እና በአሁን ወቅት የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አብዲ ረጋሳ ፖሊስ ያሉበትን እንዲያሰውቅ ጠየቀ።(አዲስ መለዳ)

……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here