የአንበሳ እና ሸገር አውቶብሶች ለታሳፋሪዎች እጅ ማጽጃ ሊያቀርቡ ነው
የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት አንበሳ እና ሸገር አውቶብሶች ለተሳፋሪዎቻቸው የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር እንደሚያቀርቡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ አስታወቁ።
ተሳፋሪዎች ወደ አውቶብሶቹ ሲገቡ እጃቸውን በሳኒታይዘር እንዲያጸዱ የሚሆኑ ገለጸ ሲሆን እንዲሁም የአውቶብሶቹ አሽከርካሪዎች የእጅ ጓንት ያደርጋሉ ሲሉም ምክትል ከንቲባው አክለዋል።
……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………
ዛሬ መጋቢት 07/2012 በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮች አንድ ዶላር በ33 ብር አካባቢ እየሸጡ መሆኑን አዲስ ማለዳ አረጋገጠች። ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸርም የአንድ በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን በጥቁር ገበያ ደግሞ አንድ ዶላር ወደ 42 ብር ገደማ እየተሸጠ እንደሆነም ማወቅ ተችሏል።በተመሳሳይ አንድ ፓውንድ በሁሉም ባንኮች እስከ 39 ብር ከ75 ሳንቲም እየተሸጠ ሲሆን አንድ ዩሮ ደግሞ 37 ብር አካባቢ በመሸጥ ላይ ነው። በተጨማሪ አንድ የኩዌት ዲናር በ102 ነጥብ 7ብር እየተሸጠ ይገኛል።(አዲስ ማለዳ)
………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………
ለቦርዱ ቴክኒካዊ ድጋፍ ከሚሰጡ የውጭ አገር ባለሙያዎች መካከል አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ ተጠረጠሩ ሲሆን ምርመራ ተደርጎ ውጤቱ እስኪረጋገጥ ድረስ ለቅድመ ጥንቃቄ ሲባል የተወሰደ እርምጃ እንደሆነ ቦርዱ አስታውቋል።ግለሰቡ ከአንድ ወር በፊት ወደ አገር ውስጥ የገባ ሲሆን ቦርዱም ምልክቶቹ ከታዩበት ጊዜ አንስቶ ምርመራ እንዲደረግለት ጠይቆ ምርመራው እንዲካሄድ እየጠበቀ እንድሚገኝም ቦርዱ ይፋ አድጓል።(ምርጫ ቦርድ)
………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………
ከዛሬ መጋቢት 07/2012 ጀምሮ ትምህርት ቤቶች፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና ትላልቅ ስብሰባዎች ለ15 ቀናት እንደሚዘጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ። የመጀመሪያ እና ኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመላ አገሪቱ ለኹለት ሳምንታት እንዲዘጉ የወሰኑ ሲሆን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደግሞ ባሉበት ቦታ ሆነው ሳይወጡ እና ሳይገቡ ክትትል እየተደረገላቸው እንዲቆዩ መወሰናቸው ተገለጸ። በእምነት ተቋማት የሚደረጉ ሰፋ ያሉ የአምልኮ ሥርዓቶች ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት እንዲቀንሱ የሚደረግበትን አግባብ የሃይማኖት መሪዎች እንዲያመቻቹም ጠይቀዋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት)
………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አምስት ደርሷል።ከዱባይ የመጣ ግለሰብ አምስተኛው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ቀደም ሲል የተለዩት አራት ታማሚዎች በአሁኑ ሰዓት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ጋር ንክኪ ነበራቸው የተባሉ 117 ሰዎች ተለይተው የቅርብ ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑንም አክለዋል።(ጤና ሚኒስትር)
………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………
አዲስ አበባ ውስጥ ‘የፊት ማስክ በ500 ብር እንሸጣለን’ በሚል በማህበራዊ ድረ ገጽ ያስተዋወቁ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአራዳ ከፍለ ከተማ ፓሊስ መምሪያ አስታወቀ።ተጠርጣሪቹ ህገ-ወጥ መድሃኒቶችን ለመድሃኒት ማስቀመጫና መሸጫ በተከለከለ ቦታ ይዘው ተገኝተዋል። የወንጀል መርማሪ ምክትል ሳጂን አዳነኝ አዱኛ ለኢዜአ እንደገለጹት ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት በማህበራዊ ትስስር ገጽ /ፌስ ቡክ/ በተጋነነ ዋጋ ‘የፊት ማስክ እንሸጣለን’ ብለው በለጠፉት ማስታወቂያ ነው።(ኢዜአ)
………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………
መቄዶንያ 102 ሚሊየን ብር ከገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙ ማግኘቱን አስታወቀ። መቄዶንያ የአረጋውያ እና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል እንዳስታወቀው በትናንትናው ዕለት መጋቢት 07/2012 በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያው ቃል የተገባለት በአጠቃላይ 102 ሚሊየን ብር እንደሆነ ገለጸ፡፡ይህም ገንዘብ በማዕከሉ ጊቢ የተጀመረውን ህንፃ 10 በመቶ እንደሚሰራለት ገልጿል። (ኢትዮኤፍኤም)



