ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቴክኒክ ድጋፍ ከሚያደርጉ የውጪ ዜጋ ባለሞያዎች አንዱ የሆነውና የኮሮና ቫይረስ መያዝ ምልክቶችን አሳቷል ተብሎ የተጠረተረው ግለሰብ ከኮሮና ቫይረስ ነጻ መሆኑን ተገለጸ።
የግለሰቡ የምርመራ ውጤት ከኮሮና ቫይረስ ነጻ መሆኑን ተከትሎ ቦርዱ ወደተለመደው የስራ እንቅስቃሴ መመለሱን አስታውቋል።
ቦርዱ ኢትዮጵያ ኮቪድ 19 ድንገተኛ ምላሽ ቡድንን እና የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ምስጋናውን አቅርቧል።



