በኢትዮጲያ ከተሞች እየታየ ያለውን የመኖርያ ቤት ችግር ለመፍታት በቀጣይ አስር አመት ውስጥ በተያዘው የቤቶች ልማት መርሃ ግብር 4ነጥብ 4 ሚሊዮን ቤቶች እንደሚገነቡ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ቤቶቹም የሚገነቡት በመንግስት ብቻ እንዳልሆነም አመላክቷል፡፡
በሚኒስቴሩ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ታደሰ ከበበ እንዳነሱት የቤቶች ልማት መርሃግብር ሪፎርም ያስፈልገዋል ተብሎ በጥናት ከተለየ በኋላ በሚቀጥሉት አስር አመታት 4 ሚሊዮን 4መቶ ሺህ ቤቶች ለመገንባት ዕቅድ ተይኋል፡፡
ከሚገነቡት 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቤቶች ውስጥ የመንግስት ሚና 20 በመቶውን ብቻ መሆኑን ነው የተገለጸው፡፡ በዚህ ውስጥ 10/90 20/80 እንዲሁም 40/60 ግንባታቸው ይቀጥላሉ፡፡ 10/90 አዲስ አበባ ላይ ቆሞ የነበረ ቢሆንም አሁን በጥናት በመለየቱ ሚቀጥል ይሆናል፡፡
እንደ አዲስ ተጨመረው ኪራይ ቤቶች በስፋት የሚገነቡ መሆናቸው የተጠቀሰ ሲሆን፤ በተቻለ መጠን ሰዎች በገቢ ልካቸው ሊከራዩ የሚችሏቸው ቤቶችን መንግስት እንዲገነባ ይደረጋል ብለዋል፡፡
በሁለተኛ ደረጃ የጠዩዡት የመሃበር ቤቶች መሆናቸውን ጠቅሰው ፤ዜጎች በመሃበር ተደራጅተው የሚገነቡት ቤት ይገነባል ከተባለው 4 ሚሊዮን ቤት 35 በመቶ ያህሉን መሆኑን ተናግረዋል ሲል አዲስ ዘመን አስነብቧል፡፡
ቅጽ 2 ቁጥር 90 ሐምሌ 18 2012



