ሳይንቲስቶች የአንበጣ መንጋ እንዲፈጠር ምክንያት የሆነውን ኬሚካል ማወቃቸውን አስታወቁ፡፡ በቀን የራሳቸውን ክብደት ያክል የሚመገቡት አንበጣዎች በብዛት ሲሰባሰቡ ሰብል ማውደማቸው በኢትዮጵያ ተከስቶ መታየቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ከቅርብ ወራት በፊት እንኳ ኢትዮጵያንና ኬኒያን ጨምሮ በበርካታ የአፍሪቃ ሀገራት ከፍተኛ የሰብል ውድመት ማድረሱ ይታወቃል፡፡
ተመራሪዎቹ ያገኙት አዲስ ግኝት አንዱ አንበጣ ከሌላ አንበጣ አጠገብ ሲሆን የሚያመነጨው መአዛ አለ፡፡ ይህ መአዛ ደግሞ ሌሎችን በመሳብ እንዲሰባሰቡ ያደርጋቸዋል፡፡ በመሆኑም በዚህ መአዛ ምክንያት አንበጣዎቹ ተሰባስበው ወደ መንጋነት ይቀየራሉ፡፡
ሳይንቲስቶቹ እንደሚሉት ይህንን መንጋ እንዲፈጠር ምክንያት የሆነውን መአዛ ማሽተት የማይችሉ አንበጦችን በዘረመል ምህንድስና በላብራቶሪ ውስጥ በማራባትና በማውጣት መንጋው እንዳይፈጠር ወይም ደግሞ ፌርሙን (መአዛ) በመጠቀም በቀላሉ በአንድ አከባቢ እንዲሰባሰቡና በቀላሉ እንዲወገዱ ለማድርግ እንዲቻል እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ቅጽ 2 ቁጥር 93 ነሐሴ 9 2012



