የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ተረኛ ምድብ ችሎት በእነ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ቀሪ ምስክሮችን መስማት ጀመረ።
ፍርድ ቤቱ ባለፈው ቀጠሮ ዐቃቤ ሕግ እና የተጠርጣሪ ጠበቆች ባቀረቧቸው አቤቱታዎች ላይ ትእዛዝ ሰጥቷል።
ጃዋር እና በቀለ ገርባ ያለ ፈቃዳችን ፎቶግራፍ እና ቪዲዮ እየተቀረጽን ስለሆነ ይህም ሊታገድልን ይገባል በማለት አመልክተዋል።
ተጠርጣሪዎቹ በችሎቱ ቤተሰቦቻችን ይግቡ የሚል አቤቱታም አንሥተዋል።
የኮቪድ-19 ምርመራ ያላደረጉ አራት ተጠርጣሪዎችም አገልግሎቱ እንዲሰጣቸው ይሁን ብለው አመልክተዋል።
ችሎቱ መገናኛ ብዙኃን ያለተጠርጣሪዎቹ ፈቃድ ለዘገባ ፎቶአቸውንና ቪዲዮአቸውን እንዳይጠቀሙ ሲል አዝዟል።
የኮቪድ-19ን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ከአራት ያልበለጡ የተጠርጣሪ ቤተሰቦች እንዲገኙ የሚለውንም በትእዛዙ አካትቷል።
ከሃይማኖት አባቶቻቸው እና ከጠበቆቻቸው ጋር ለ40 ደቂቃ ያህል ተገናኝተው እንዲያወሩም ችሎቱ አዟል ሲል ፋና ዘግቧል።



