በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ ተሸክርካሪ ይበዛባቸዋል ተብለው በተለዩ ቦታዎች ላይ ከተሸከርካሪዎች በሚወጡ ጭሶች ምክንያት የአየር ብክለት መጠን የዓለም ጤና ድርጅት ካስቀመጠው መስፈርት በላይ መሆኑ ታወቀ።
በመገናኛ፣ ፒያሳ፣ መርካቶ፣ ጎሮ፣ አውቶብስ ተራ፣ ጦርኃይሎች አካካበቢ በሚገኙ የታክሲ ፌርማታ እና አውቶብስ ፌርማታ በአጠቃላይ 20 በሚሆኑ ቦታዎች ላይ በተደረገው ጥናት በከባቢ አየር ውስጥ ከ20 እስከ 35ነጥብ5 ማይክሮ ግራም ፐር ኪዩብ ለጤና ጎጂ የሆኑ ብናኞች መገኘታቸውን የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።
የዓለም የጤና ድርጅት ያቀመጠው መስፈርት 10 ማይክሮ ግራም ሲሆን በአዲስ አበባ ከላይ የተጠቀሰው ቁጥር ከደረጃ በላይ በመሆኑ በጤና ላይ ሊደርስ የሚችለውን ችግር አሳሳቢ እንደሆነ የሚያመላክት መሆኑን የኮሚሽኑ የአካባቢ ንብረት ‹‹ሚኒስትሪሚንግ›› ቡድን መሪ የሆኑት ፋንቱ ክፍሌ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
ጥናቱ በኹለት ዓይነት መንገድ የተደረገ ሲሆን አንደኛው ተንቀሳቃሽ መሳሪያ በመጠቀም ተሸከርካሪዎች ይበዙባቸዋል ተብለው በተመረጡ ቦታዎች የተደረገ ሲሆን፤ ኹለተኛው ደግሞ የመኪና ጭስ ማውጨ ለይ ተገጥሞ የሙቀት ዓማቂ ጋዞች መጠናቸው ምን ያህል እንደሆነ የሚለካ እንደሆነም ፈንቱ ተናግረዋል።
ፋንቱ እንሚያስረዱት ከሆነም የጥናቱ አስፈላጊነት የአየር ንብረት ለውጥ ሙቀት አማቂ ጋዞች ላይ ሥራዎች በሚሰሩበት ሰዓት የተቀመጡ እና የተጠኑ መረጃዎች ባለመኖራቸው የመረጃ ክፍተት ለምፍታት እንደሆነም አስረድተዋል።
ጥናቱ የተደረገው ከC 40 Cities Climate Leadership Group በተገኘው የ50 ሺህ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ሲሆን ከድጋፉ ግማሹ ወጪ የተሸፈነው መመርመሪያ መሳሪያዎችን ከውጭ አገር ገዝቶ ለማስመጣት እንደዋለ ነው ፋንቱ የሚገልጹት።
ሚኒባስ፣ ኋላ ክፍት ተሸከርካሪ፣የቤት አውቶሞቢል፣ አውቶብስ እና ከሁሉም ዓይነቶች ተሸከርካሪዎች የመለከኪያ መሰፈርት በመጠቀም ናሙና መወሰዱን የገለጹት ፋንቱ ተሽከርካሪዎች የተመረቱበትንም ጊዜ በጥናቱ ውስጥ ሊካተቱ እንደቻሉም ጠቁመዋል።
ከ1992 በፊት የተመረቱ ተሸከርካሪዎችም ውስጥ ለጤና ጎጂ የሆኑ ብናኞች እና ኬሚካሎች የተገኙ ሲሆን ይህም በሰው ልጆች ላይ የመተንፈሻ አካላቸው ላይ የጤና ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ መሆናቸውን ኮሚሽኑ በግኝቱ ላይ አስፍሯል።
ከ1992 እስከ 20014 በተመረቱ ተሸከርካሪዎች ላይ በተወሰደው ናሙና ከ72 እስከ 74 ማይክሮ ግራም ፐር ሜትር ኪዩብ ከፍተኛ ሊባል በሚችል ከባቢ አየርን የሚበክሉ ኬሚካሎች እና ጋዞችን ወደ ከበባቢ አየር የሚለቁ ሆነው አግኝተናቸዋል ሲል ከሚሽኑ አስታውቋል።
ከ2014 በኋላ በተመረቱ ተሽከርካሪዎች ውስጥ ደግሞ 50 ማይክሮ ግራም ፐር ሜትር ኪዩብ ብናኝን ወደ ከካቢ አየር እድሚለቁ ጥናቱ አመላክቷል።
የችግሩን አሳሳቢነት እና በጤና በኩል የሚያደርሰው ችግር ለመከላል በመንግስት በኩል ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ተሸከርካሪዎች መቀነስ፣ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ ማስገባት፣ እንደ ብስክሌት ያሉ መገልገያዎችን ማብዛት ፣የቀላል ባቡር ግንባታዎችን በማከናወን ችግሩን ማቃለል እንደሚቻል ፋንቱ አሳስበዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ሰኔ 2012 ድረስ ባለው መረጃ ከ63 ሺ በላይ ተሽከርካሪዎች እንደሚገኙ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከሁለቱ ማለትም ከሀረሪ እና ከትግራይ ክልሎች ውጪ ዓመታዊ የተሽከርካሪ ብዛት 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን መድረሱን የባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ይግዛው ዳኜ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።
ቅጽ 2 ቁጥር 95 ነሐሴ 23 2012



