የኢትዮጵያ አየር መንገድ 14 አዉሮፕላኖች ዳግም ለመንገደኛ አገልግሎት ዝግጁ አደረገ

0
1035

በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ወረርሽ ከተከሰተ በኋላ ከህዝብ ማመላሻነት ወደ ዕቃ ጫኝነት ከተቀየሩት 25 አውሮፕላኖች መካከል 14ቱ ዳግም ለመንገደኞች ዝግጁ መሆናቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአዲስ ማለዳ ገለጸ።

አብዛኞቹ የዓለማችን አገራት የአየር ክልላቸውን በመዝጋታቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድም የህዝብ ማመላሻ የነበሩትን አውሮፕላኖች ወደ ካርጎ አገልግሎት ማዋሉ የሚታወስ ሲሆን በአሁን ወቅት ደግሞ አገራቱ የአየር ክልላቸውን በመክፈታቸው አውሮፕላቹን ከካርጎ ዳግም ወደ ሕዝብ ማመላሻነት እየተቀየሩ መሆናቸውን ኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል።

በአሁን ወቅት 14 አውሮፕላኖች ለመንገደኞች ዝግጁ ተደርገው በመመለስ እና ለሕዝብ ማመላለሸነት እንዲሆን ወይም ለመንገደኞች በረራ እየተዘጋጁ እንደሆነ አየር መንገዱ አስታውቋል።

እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጻ ከሆነም 11 የመንገደኛ አውሮፕላኖች የነበሩት ደግሞ ወደ እቃ ጫኝነት በመቀየር አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል።

አውሮፕላኖቹን ከሕዝብ ማመላለሻነት ወደ ዕቃ ጫኝነት ሲቀየሩ ሥራው ሙሉ በሙሉ በአየር መንገዱ የቴክኒክ ባለሙያች የተሸፈነ ሲሆን በዚህም መሰረት 1ነጥብ8 ሚልዮን ዶላር ወጪ ማዳናቸውን አየር መንገዱ ጠቅሷል። በመሆኑም አውሮፕላኖቹን ከህዝብ ማመላሻ ወደ ካርጎ ሲቀየሩ የሚወስደው ጊዜ እንደ አውሮፕላኑ አይነት የሚለያይ ቢሆንም ባማካይ ከ24 እስከ 36 ሰዓታት እንደወሰደ ተገልጿል።

ከዕቃ ጫኝነት ወደ ሕዝብ ማመላለሻነት የተቀየሩት ደግሞ እንደ አውሮፕላኑ አይነት የሚለያይ ቢሆንም በአማካኝ ከ48 እስከ 72 ሰዓታት ይፈጃል ተብሏል።
ከካርጎ ወደ ሕዝብ ማመላነሻነት የተቀየሩት 14ቱ የአውሮፕላን ዓይነቶች ቦይን 777-300፣ ቦይንግ 767-300፣ቦይንግ 737-800፣ እና Q400 መሆናቸውን ነው አየር መንገዱ ለአዲስ ማለዳ ያስታወቀው።

በአጠቃላይ በዚህ ሥራ ላይ 25 የሚሆኑ የአየር መንገዱ የአውሮፕላን ጥገና ባለሙያዎች እንደተሳተፉበት ከአየር መንገዱ ለማወቅ ተችሏል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው ወረርሽኝ መሰረት የአየር እንቅስቃሴዎች መገታታቸውን ተከትሎ በርታ አየር መንገዶች ከፍተኛ ኪሳራ ላይ ወድቀው የነበረ ሲሆን አየር መንገዱ ግን የአገልግሎት ዘርፋቸውን በመቀየር መጣ ከነበረው ከፍተኛ ኪሳራ መዳኑን ለማወቅ ተችሏል።

በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያስገነባው አዲሱ የተሳፋሪዎች ተርሚናል ግንባታ ግንባውን ማከናወን ያስፈለገበት ምንክንያትም የመንገደኞች ቁጥር እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በርካታ መንገደኞችን ላማስናገድና አካላዊ መራራቅን ተግባራዊ ለማድረግ ታስቦ በቴክኖሎጂ የታገዙ ኪዮስኮችና መንገደኞች ትኬት ከመቁረጥ አውሮፕላን እስከ መሳፈ ር ድረስ ያለ ምንም አካላዊ ንክኪ በራሳቸው እንዲከውኑ ተደርጎ የተሰራ መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል።

ግንባታውን ያከናወነው CCCC የተባለ የቻይና ኩባንያ ሲሆን ተርሚናሉ በዓመት 22 ሚልዮን መንገደኞችን ማስተናገድ እንደሚችል አየር ምጉ ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል።

አየር መንገዱ ስለ ባዮ ሴኩሪቲ እና ባዮ ሴፍቲ ሲያብራራም ‹‹የተጓዦችን የጤና ደህንነት ከማስጠበቅ ጋር የተያያዘ ጽንሰ ሃሳብ ነው።ይልቁንም ጽንሰ ሃሳቡን በኮቪድ 19 ወረርሺኝ አውድ ውስጥ ስንመለከተው በአየር ማረፊያና በበረራ ወቅት የምንሰጠው የደንበኞቻች አገልግሎት የተጓዦችን የጤና ደህንነት በሚያረጋግጥ መልኩ መሰጠት እንዳለበት ያመለክታል።›› ብሏል።

ቅጽ 2 ቁጥር 98 መስከረም 9 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here