‹‹የ ሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና የሚሰጥበት ሂደት እኛ እንድንጎዳ ያደርገናል›› ተማሪዎች

0
787

በ2012 አገር ዐቀፍ የኹለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና የተቀመጠው ቅድመ ሁኔታ በኢትዮጲያ ያለውን የኢንተርኔት አስተማማኝነት እና የተማርንበትን ጊዜ ያላማከለ ነው ሲሉ የ12 ክፍል ተፈታኞች ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ፡፡

ተማሪዎቹ በከፍተኛ ሁኔታ ስጋት ውስጥ ነን በማለት ከገለፁት ምክንቶች መካከል አንደኛው  የኢንተርኔት አገልግሎቱ ሲሆን፤ ሁሉን ተቋቁመን እንፈተን እንኳ ብለን ብንወስን ከዚህ በፊት ከቴክኖሎጂ ጋር ያለን ቅርበት ግምት ውስጥ አለመግባቱ ዋናው ተግዳሮት  ነው ብለዋል፡፡

ከዛም ባሻገር ‹‹ትምህርት ሚኒስቴር እንዴት አስቦት እንደሆነ ባላውቅም የአገር ዐቀፍ የኹለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ለክልልም ለከተሞችም በእኩል ሰዓት የሚሰጥ እንደመሆኑ አንዳንድ ቦታ የመቋረጥ  ችግር ቢያጋጥም ትምህርት ሚኒስቴር እንዴት ሊፈታው ነው›› በማለት የገለፀልን ለደኅንነቱ ሲባል ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ተፈታኝ ተማሪ ‹‹ የኛን ህይወት እንደማበላሸት ነው የምቆጥረው››ሲል ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም የ 11ኛ ከፍል ሙሉ ትምህርቱ እና የ 12ኛ ክፍል  ደግሞ የስድስት ወር ትምህርት በቀረው አጭር ጊዜ ውስጥ እንዴት  ድጋሚ ተሸፍኖ ሊያልቅ ነው ሙሉውን በፈተናው  የሚካተተው በማለት ያነሱ ሲሆን ፤  ለአምስት ሳምንታት እንዲሰጥ የተወሰነው ከፈተና በፊት የክለሳ ትምህርትም አስካሁን አለመጀመሩ ሌላኛው ግርታን እየፈጠረብን ያለ ነገር ነው በማለት ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እና አስካሁን ስጋት ውስጥ በመሆናችን ምክንያት ደግሞ በየትምህርት ቤቶቻችን የትምህርት ክለሳ እና መሰረታዊው ኮምፒውተር ስልጠናው መቼ እንደሚጀመር ደጋግመን በስልክም በአካልም እየጠየቅን ቢሆንም ትምህርት ቤቶቻችን ግን ‹‹መቼ እንደሚሰጥ  ለኛም የተረጋገጠልን ነገር የለም ›› በማለት እንደሚመልሱላቸው ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር መረጃ በመፈለግ ደጋግመን  ብንደውልም መልዕክት ብንልክም ማግኘት አልቻልም፡፡ ከዛም በተጨማሪ ለሳምንታት የትምህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት  ሃረጓ ማሞ ወልደ ሚካኤል ጋር በእጅ ስልካቸው ደውለን መልዕክት ልክን  የነበረ ቢሆንም ‹‹አሁን ስብሰባ ላይ ነኝ ምላሽ መስጠት አልችልም›› በማለታቸው ሳይሳካልን ቀርቷል፡፡

ነገር ግን የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ህዳር 22 እና 23፤ የ12ኛ ክፍል ፈተና ደግሞ ከህዳር 28 እስከ ታህሳስ 1 እንዲሰጥ የሚል ምክረ ሀሳብ መቅረቡ እና ለዚያም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጾ ነበር።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መውሰድ የሚችሉት የ11ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀቁና የ12ኛ ክፍልን የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ ብቻ ናቸው ተብሏል። የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሕዳር 28 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2013  እንደሚሰጥም በምክረ ሀሳቡ ላይ ተጠቅሷል።

ነገር ግን እነዚህ ምክረ ሃሳቦችም እንደ ሁኔታው ተፈፃሚ ላይሆኑ የሚችሉበት አማራጭ ተቀምጠዋል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር ከቀናት በፊት እንደገለፀው የ12ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና በተያዘለት ጊዜ ለመስጠት ትምህርት ቤቶች ኮቪድ-19 መከላከል መሰረት ያደረጉ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል። የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እና ምዝገባ በኦንላይን እንደሚካሄድ እና ተማሪዎች የ45 ቀን የማካካሻ እና የቴክኖሎጂ መለማመጃ ጊዜም እንደሚሰጣቸው የትምህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሃረጓ ማሞ ተናግረው ነበር።

ስለዚህም ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱት እና ፈተናም የሚሰጠው አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ማሟላት ሲችሉ ብቻ መሆኑም ተገልጿል። ይህ  መሆኑ እና የተረጋገጠ ነገር አለመነገሩ ደግሞ ተፈታኝ ተማሪዎቹ ከፍተኛ ጥርጣሬ እና መጨናነቅን እንደፈጠረባቸው ለአዲስ ማለዳ አስረድተዋል፡፡

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here