መዝገብ

Author: ረድኤት ገበየሁ

በኢትዮጵያ የኦክስጅን ቬንትሌተር መመረት ሊጀምር ነው

በዓለም ላይ ከኮሮና ወረርሽኝ ተጠቂዎች መብዛት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ እጥረት የታየበት የኦክስጅን ቬንትሌተር በኢትዮጵያ ለማምረት ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ። ይህም ኒው ኤራ ሪሰርች ዴቨሎፕመንት (ነርድ) በተባለ አገር በቀል ኩባንያ በኢትዮጵያ ውስጥ መመረት ሊጀምር መሆኑ ታውቋል። የኩባንያው ዋና ሥራ አስኪያጅ ናትናኤል ከበደ…

የበረሃ አንበጣ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ተገለጸ

በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከተከሰተው የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ በበለጠ አዲስ የአንበጣ መንጋ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቀው፣ የአንበጣ መንጋ ከዚህ ቀደም ባልተከሰተባቸው አካባቢዎች የመከሰት አዝማሚያ በማሳየቱ እና መጤ ባለመሆኑ የሚያደርሰውን ጉዳት ያከፋዋል። የግብርና ሚኒስቴር ሕዝብ ግንኙነት…

በአዲስ አበባ ሰው ሠራሽ የምግብ ዘይት እጥረት ተከሰተ

የምርት ወይም የአቅርቦት እጥረት ባልተከሰተበት ሁኔታ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የተከሰተውን ወረርሽኝ ተከትሎ የምግብ ዘይት ዋጋ ይጨምራል በሚል በነጋዴዎች ዘንድ ያለአግባብ ዘይት በመደበቅ ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ የምግብ ዘይት እጥረት መፈጠሩን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ። ሚኒስቴሩ ጨምሮ እንደገለጸው፣ የምግብ…

በአዲስ አበባ የጎዳና ተዳዳሪዎችን በቋሚነት ወደ መጠለያ ለማስገባት እየተሠራ ነው

በከተማዋ 52 ሺሕ የሚደርሱ የጎዳና ተዳዳሪዎች ይገኛሉ። የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ 52 ሺሕ ለሚደርሱ የጎዳና ተዳዳሪዎች በቋሚነት መጠለያ በማዘጋጀት ላይ እንደሆነ አስታወቀ። ሚኒስቴሩ ጨምሮ እንደገለጸው፣ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተከትሎ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ተጋላጭነት ለመቀነስ እየተሠራ ቢሆንም፣ ከወረርሽኙ ባለፈ…

በአዲስ አበባ የታክሲዎችን እንቅስቃሴ የሚቆጣጠር መተግበሪያ ወደ ሥራ ሊገባ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ የሚንቀሳቀሱ የከተማ ታክሲዎችን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የሚረዳ ‹አዲስ ጉዞ› የተሰኘ አዲስ መተግበርያ በሥራ ላይ ለማዋል በሂደት ላይ እንደሆነ ተገለጸ። አዲሱ የታክሲዎች መቆጣጠሪያ መተግበሪያ የትራንስፖርት አመራር ስርዓት (TMS) አገልግሎትን የሚያሳልጥ ሲሆን፣ ከ15 ቀን በኋላ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅቶች…

የግል ድርጅቶች የሠራተኞችን ጡረታ በተገቢው መንገድ እያስገቡ አይደለም

የግል ድርጅቶች የሠራተኞቻቸውን የማኅበራዊ ዋስትና ገንዘብ በተገቢው መንገድ እየከፈሉ እንዳልሆነ የግል ድርጅቶች የማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ። ከዚህ ቀደም ይህን መሰል ችግሮች በተደጋጋሚ ይስተዋሉ የነበረ ሲሆን፣ ነገር ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን ኤጀንሲው ለአዲስ ማለዳ ገልጿል። ተገቢውን ክፍያ…

አራት መቶ ሚሊዮን ብር የተመደበለት የበቆጂ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት መጓተቱ ተገለፀ

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የበቆጂ የውሃ ሥራ ፕሮጀክት መጀመር ከነበረበት ጊዜ በአምስት ወራት መጓተቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገለፁ። የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮው ከኹለት ዓመታት በፊት ተጀምሮ የተተወ ቢሆንም በ2012 መጀመሪያ ላይ ግን 400 ሚሊዮን ብር ተመድቦለት መስከረም ላይ ወደ ሥራ…

በዘውዲቱ ሆስፒታል ባጋጠመ የሕክምና ስህተት በአንዲት ታዳጊ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ

በዘውዲቱ ሆስፒታል በተፈጠረ የሕክምና ስሕተት ምክንያት ነኢማ ሻሚል በተባለች የሰባት ዓመት ታዳጊ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ። ከስድስት ወራት በፊት ትርፍ አንጀት ታማ ወደ ሆስፒታሉ የገባችው ታዳጊዋ ነኢማ፣ ቀዶ ጥገና ቢሠራላትም ግራ ትከሻዋ ላይ፣ ቀኝ እጇ ላይ፣ ቀኝ እግሯ ላይ እንዲሁም…

የመጀመሪያው የዲያስፖራ ባንክ አክሲዮን መሸጥ ጀመረ

በዓለም ዐቀፉ ውድድር ላይ የራሱን ፈተና ይዞ መምጣቱ አይቀርም የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ባንክ 70 በመቶ አባላቱን በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በማድረግ እና ቀሪውን ከአገር ውስጥ በማሰባሰብ፣ በአጠቃላይ ስድስት ቢሊዮን ብር ካፒታል አዲስ ባንክ ለማቋቋም ፈቃድ አግኝቶ ከመጋቢት 4/2012 ጀምሮ አክሲዮን መሸጥ ጀመረ።…

ፕራይም የተሰኘ አዲስ የቴሌቪዥን ጣቢያ የሙከራ ስርጭት ጀመረ

‹‹የኛ ሚዲያ በምክንያት የሚወግን ይሆናል›› ፕራይም ሚዲያ የተባለ አዲስ የቴሌቭዥን ጣቢያ ከብሮድካስት ባለሥልጣን ፈቃድ ተሰጥቶት ረቡዕ መጋቢት 2/2012 የሙከራ ስርጭቱን ጀመረ። ጣቢያው መደበኛ ስርጭቱን ሲጀምር የሚጠቀመው የስርጭት ቋንቋ ስዋሂሊን ሲሆን፣ በተጨማሪ በምሥራቅ አፍሪካ ብዙ ተናጋሪ ያላቸው ቋንቋዎች እንደሚሆን አስታውቋል። ብርሃኑ…

‹‹በቢራ እጣዎች መቆም ገቢዬ ቢቀንስም ከውርርድ ያገኘሁት ገቢ ጨምሯል›› ብሔራዊ ሎተሪ

የብሔራዊ ሎተሪ የ2012 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የተጣራ ትርፍ 108 ሚሊዮን ብር በመሆን ተመዝገበ። ይህም ገቢ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በስድሰት ሚሊዮን ብር ቅናሽ ቢያሳይም፣ ከውርርድ የተገኘው ገቢ ትርፉ ከዚህ በላይ እንዳያሽቆለቁል እንዳደረገው ተቋሙ አስታውቋል። በስድስት ወር ውስጥም 492 ሚሊዮን…

ኢትዮ ስኳር መንግሥት እጁን ከስኳር ፋብሪካዎች ላይ ያንሳ ሲል ጠየቀ

መንግሥት ሦስት በማምረት ላይ ያሉ የስኳር ፋብሪካዎችን ወደ ግል ዘርፍ ለጊዜው አላዞርም ማለቱን አግባብ አይደለም ሲል ከእነዚህ ፋብሪካዎች ውስጥ መተሃራ ስኳር ፋብሪካን ለመግዛት አንድ ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር አክስዮን የሸጠው ኢትዮ ስኳር አክሲዮን ማኅበር ተናገረ። ‹‹እኛ የምንረዳው ጨረታ ላይ የማውጣት…

ሰባት ወራት የፈጀው የሎጂስቲክ ሕንፃን የማፍረስ ሙከራ አስቸጋሪ ሆኖ ቀጥሏል

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት በመሆን ለ21 ዓመታት ያገለገለው ሕንጻ፣ ለለገሃር የተቀናጀ ልማት የቤቶች ግንባታ ታስቦ እንዲፈርስ ተወስኖ ለሰባት ወራት ሙከራ ቢደረግም እስከ አሁን ሙሉ ለሙሉ ማፍረስ ሳይቻል ቀጥሏል። ስምንት ወለል ወደ ላይ የሚረዝመው እና ከምድር…

አሕመድ ቱሳ የነዳጅ አቅርቦት እና ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ኃላፊ ሆነው ተሾሙ

የማዕድን እና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የንግድ ሚኒስቴር ለዓመታት ሲያወዛግብ የቆየውን የነዳጅ ስርጭት ችግሮችን ለመቆጣጠር የተቋመውን የነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትና ስርጭት ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን እንዲመሩ አሕመድ ቱሳ ተሾሙ። መቋቋሚያ አዋጁ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀ ከወራት በኋላ የሰው ኃይሉን መልምሎ ወደ ሥራ…

ኖርዝ ሰታር አየር መንገድን ለመመሥረት 40 ሚሊዮን ብር አክሲዮን ተሸጠ

የትግራይ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዓለም ዐቀፍ አገልግሎት የሚሰጥ ኖርዝ ስታር የተሰኘ የአየር መንገድ ለማቋቋም አክሲዮን መሸጥ የጀመረ ሲሆን፣ በዚህም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ 40 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ሽያጭ ማከናወኑን ገለፀ። የኖርዝ ስታር አየር መንገድ የቦርድ አባል እና አመራር የሆኑት መኮንን አሰፋ…

ምርጫ ቦርድ ክስ ተመሠረተበት

የቀድሞ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢዴፓ/ ፕሬዝዳንት እና የአሁን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ምክትል ሊቀ መንበር ጫኔ ከበደ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተደራቢ የፖለቲካ ሥያሜ አሁን እየተንቀሳቀሰ ላለው ኢዴፓ መስጠቱ አግባብ አይደለም በሚል ክስ መሰረቱ። ሰኞ የካቲት 23/2012 በፌደራሉ…

ዳግም የተከሰተው የበረሃ አንበጣ ስኳር ፋብሪካዎችን ስጋት ላይ ጥሏል

ባለፈው የዝናብ ወራት ተከስቶ ከዚያም ወደ ጎረቤት አገራት ሸሽቶ የነበረው የአንበጣ መንጋ፣ በተለያዩ አቅጣጫዎች በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ መግባት መጀመሩ የስኳር ፋብሪካዎችን አደጋ ላይ ሊጥላቸው እንደሚችል ታወቀ። ከሦስት ሳምንት በፊት በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የሚተዳደር 240 ሄክታር የሸንኮራ ማሳ ላይ የበረሃ…

የትግራይ ንግድ ምክር ቤት የወልቃይት የስኳር ፋብሪካን ለመግዛት ሀብት ማሰባሰብ ጀመረ

ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች መካከል የሆነውን የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ወደ ግል ይዘዋወራሉ ተብለው ከሚጠበቁ ፋብሪካዎች መካከል መሆኑን ተከትሎ፣ የትግራይ ንግድ እና ዘርፉ ማኅበራት ምክር ቤት ሀብት በማሰባሰብ ለመግዛት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ። የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት አሰፋ ኃይለ ሥላሴ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት፣ የአዋጪነት…

መንግሥት ማዳበርያ አስኪያስገባ አስመጪዎች የወደብ እንዲከፍሉ ተገደዱ

ማዳበሪያውን ማስገባት ለሚቀጥሉት ኹለት ወራት ይቀጥላል የኢትዮጵያ መንግሥት 1.5 ሚሊዮን ቶን ማዳበሪያ እያስገባ መሆኑን ተከትሎ በጅቡቲ ወደብ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ የነበሩ ኮንቴይነሮች የወደብ ኪራይ እየከፈሉ በጅቡቲ ወደብ እንዲቆዩ ተደርገዋል። ማንነታቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ በአስመጪ እና ላኪነት ሥራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ17 ሺሕ ሠራተኞቹ የብድር አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ከአፍሪካ በትርፋማነቱ ቀዳሚ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ17 ሺሕ በላይ ሠራተኞቹን ተጠቃሚ የሚያደርግ የብድር አገልግሎች መጀመሩን አዲስ ማለዳ አረጋገጠች። ባንኮች ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት በገጠማቸው ወቅት ተግባራዊ የተደረገው አገልግሎቱ፣ ከታችኛው የሥራ መደብ እስከ ከፍተኛ ሥራ ኃላፊዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይጠበቃል። አየር መንገዱ…

የኤክሳይስ ታክሱን አዋጅ መጽደቅ ተከትሎ ዋጋ መጨመሩ የሕጋዊነት ጥያቄ አስነሳ

‹‹ ሕጉ ተፈፃሚ እንዲሆን አያስገድድም›› የኤክሳይስ ታክሱ አዋጅ የካቲት 5/2012 በተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁን ተከትሎ ታክሱ በተጣለባቸው እንደ ቢራ ያሉ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መደረጉ የሕግ አተገባበር ጊዜውን የጠበቀ አይደለም ተባለ። የታክስ ጉዳዮች እና የሕግ ባለሙያ የሆኑት ዮሐንስ ወልደገብርኤል…

ጁነዲን ሳዶ ሸገር የተሰኘ አዲስ ባንክ ሊመሠርቱ ነው

የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጁነዲን ሳዶ ‹ሸገር› የተሰኘ አዲስ ባንክ ከሌሎች አጋሮቻቸው ጋር በመሆን በማቋቋም ላይ መሆናቸውን አስታወቁ። የባንኩ መሥራች ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ጁነዲን ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት፣ ድርሻ የመሸጥ ፈቃድ ከብሔራዊ ባንክ አግኝተው ከየካቲት ሰባት ጀምሮ በይፋ አክስዮን መሸጥ…

ኤጄቶ የሲዳማ ክልል ርክክብ እስከ የካቲት 15 እንዲካሄድ ጠየቀ

እስከ የካቲት 15 ድረስ የሥልጣን ርክክብ ተካሂዶ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምስረታ የማይከናወን ከሆነ የሲዳማ የወጣቶች ቡድን የሆነው ኤጄቶ ተቃውሞ እንደሚያስነሳ አስጠነቀቀ። ሲዳማ ዞን ከደቡብ ክልል ወጥቶ ራሱን የቻለ ክልል መሆኑን በድምጹ ካረጋገጠ ሦስት ወራት ቢቆጠሩም ገዢው ፓርቲ የሲዳማን ክልል…

የሜቴክ ሰራተኞች አራት መኪኖች አቃጠሉ

የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የቢሾፍቱ ባስ መገጣጠሚያ ሠራተኞች የተገባልን የደሞዝ ጭማሪ ይፈፀምልን በሚል ምክንያት ከሦስት ሳምንት በፊት አራት አውቶቡሶችን አቃጠሉ። ከ 10 ሺሕ በላይ ሠራተኞች ያሉት ድርጅቱ በተደጋጋሚ የደሞዝ ጭማሪ እንደሚያደርግ ለሠራተኞቹ ቃል ቢገባም መፈፀም አልቻለም። በዚህ ምክንያት…

በኢትዮጵያ የሚነሱ ግጭቶችን በየሦስት ወሩ መተንተን ሊጀመር ነው

የኢትዮጵያ ስትራቴጂክ ተቋም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን በየሦሰት ወሩ የሚመዘግብ፣ የሚተነትን እና ይፋዊ ሪፖርት የሚያወጣ አዲስ ቡድን አደራጅቶ ወደ ሥራ ሊያስገባ መሆኑን ገለጸ። የመንግሥት ተቋማት፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የተለያዩ የግል ድርጅቶች እንዲሁም የሚዲያ ተወካዮች በዚህ ሥራ የሚሳተፉ ሲሆን፣ በተለያዩ ዘዴዎች…

አንድ የመሥሪያ ቦታ ለኹለት ኢንተርፕራይዞች መሰጠቱ እያወዛገበ ነው

በቦሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ አንድ የአፈር መድፊያ ቦታ በማስተዳደር ሥራ ላይ የተሰማሩ ኹለት ኢንተርፕራይዞች ተመሳሳይ ቦታ ላይ ሕጋዊ ፈቃድ ይዘው መገኘታቸው ግርታ ፈጥሯል። የእነ መስፍን ኢንተርፕራይዝ እና የተከሰተ ዮሐንስ እና ጓደኞቹ ኢንተርፕራይዝ የተባሉ በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች፣ በቡልቡላ አካባቢ…

በሰላም ሚኒስቴር የአደረጃጀት ለውጥ ምክንያት 450 ሚሊዮን ብር ወደ ሥራ አልገባም

እንደ አዲስ ከተዋቀረ አንድ ዓመት የሞላው የሰላም ሚኒስቴር ስር የሚገኘው የክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢ ድጋፍ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት፣ በድጎማ እንዲያከፋፍል የተሰጠውን 450 ሚሊዮን ብር የመዋቅር ሥራውን ባለማጠናቀቁ ምክንያት ማከፋፈል አልቻለም። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በአዋጅ ከተሰጡት ሥልጣኖች መካከል የሆኑት የፌዴራሊዝም እና አርብቶ…

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የትዊተር ገፅ 20 በመቶ ተከታዮች በማሽን የተፈበረኩ ሐሰተኛ አካውንት መሆናቸው ተገለፀ

የመብቶችና ዴሞክራሲ ብልጽግና ማእከል (ካርድ) ከትዊተር ኦዲት አገኘሁት ባለው ጥናት መሰረት፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የግል የትዊተር አካውንትን ከሚከተሉ ከ100 ሺሕ ተከታዮች መካከል 80 በመቶው ትክክለኛ ተከታዮች ሲሆኑ 20 በመቶው ግን ትዊተር ቦት ወይም በማሽን የሚፈበረኩ ሐሰተኛ አካውንቶች መሆናቸውን አስተወቀ።…

የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድ ወገንተኛ ነው ሲሉ ወቀሱ

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አድልኦ ያደርገብናል፣ ሕጋዊ እርምጃዎችን አይወስድም እና ከምርጫው በፊት የሚደረጉ ውይይቶችንም ለማድረግ ፈቃደኛ አልሆነም ሲሉ ወቀሱ። ምክር ቤቱ ከ107 አባል ፓርቲዎቹ ውስጥ ከግማሽ በላዩ የተስማማባቸውን አቋሞች አርብ 22/2012 በራስ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ…

አርሶ አደሮች መሬታቸውን ለብድር የሚያስይዙበት አገልግሎት ተጀመረ

አርሶ አደሩ ብድሩን ካልመለሰ መንግሥት እስከ 30 ዓመት ድረስ መሬቱን በማከራየት ብድሩን ያስመልሳል የይዞታ ማረጋገጫ ላላቸው አርሶ አደሮች መሬታቸውን እንደ ማስያዣ በመጠቀም በአነስተኛ የፋይናስ ተቋማት አማካኝነት እስከ 100 ሺህ ብር ድረስ ብድር የመስጠት ሥራ በአማራ፣ ኦሮሚያና እና ደቡብ ክልሎች ላይ…

This site is protected by wp-copyrightpro.com