በአገር ውስጥ ያሉ የዶሮ አርቢዎች ቁጥር ከግማሽ በታች ቀንሷል

0
1479

ደረጃ አንድ የሚባሉ ዶሮ አርቢዎች በተለያዩ ችግሮች ምንያት ከአምስት ዓመት በፊት ቁጥራቸው 21 የነበረ ቢሆንም አሁን ሰባት ያህል ብቻ መቅረታቸውን የኢትዮጵያ የዶሮ አርቢዎች ማሕበር ፕሬዝዳንት ገነነ ተስፋየ ለአዲስ ማለዳ አስታወቁ።
አንድ የዶሮ እርባታ ማዐከል ያለው ሰው ከ70-75 በመቶ የሚሆነው ወጭው የዶሮ መኖ መሆኑን ገልጸዋል። በቆሎ ዋነኛ የሚባል የዶሮ መኖ ሲሆን አሁን ባለንበት ወቅት የምርት መሰብሰቢያም በመሆኑ አንድ ኩንታል ወይንም 100 ኪሎ ግራም በቆሎ ከ500 እስከ 600 ብር መሸጥ የሚገባው ቢሆንም እየገዛን ያለነው 1 ሺሕ 100 ብር ነው ብለዋል።

ሌላኛው የዶሮዎች መኖ የሆነው የአኩሪ አተር ፋጉሎ ወይንም ከአኩሪ አተር ዘይት ከተጨመቀ በኋላ የሚገኘው ተረፈ ምርት መንግሥት ወደ ውጭ አገር ለመላክ በመወሰኑ እና ሻጮቹ ከብር ይልቅ በዶላር ቢሸጡ ስለሚያዋጣቸው ወደ ውጭ አገራት መላክ በመጀመራቸው እንዲሁም የኑግ ፋጉሎ ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት የዶሮ መኖ 62 በመቶ ጭማሪ አድርጎብናል ሲሉ ገልጸዋል። ይህ ደግሞ የዶሮ እና የእንቁላል ምርት አቅራቢዎች ያወጡትን ወጭ አስልተው ለገበያ ለማቅረብ ካስቀመጡት ዋጋ ጋር ስለማይመጣጠን የእንቁላል ዋጋ በእጥፍ ሊጨምር ይችላል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎች ማሕበር ውስጥ 98 ያሕል አባላት እንዳላቸው ገልጸዋል። በማሕበሩ አባል ለመሆን ደረጃ አንድ ወይንም ከፍተኛ ዶሮ አርቢ መሆን ወይንም መካከለኛ ዶሮ አርቢ መሆን እንደሚጠይቅ ተናግረዋል። ከፍተኛ እና መካከለኛ ዶሮ አርቢዎች ቫት ተመዝጋቢ መሆናውን አሳውቀዋል።

ከውጭ አገር የተሻሻሉ የዶሮ ዝርያዎችን የሚያስመጡ የዶሮ መኖ ማቀነባበሪያ ያላቸው እና የራቸው የዶሮ ማስፈልፈያ(ኢንኩቤተር) እና ማባዣ ማዐከላት ያላቸው አንደኛ ደረጃ ዶሮ አርቢዎች እንደሚባሉ የኢትዮጵያ የዶሮ አርቢዎች ማሕበር ገልጿል።
አክውም እነዚህ ዶሮ አርቢዎች በተለይ ደግሞ የዶሮ ማስፈልፈያ እና ማባዣ ማዐከላ ያሏቸው ተዘጉ ማለት ከውጭ አገራ የዶሮ ዝርያ የሚያመጣ የለም ማለት ነው ብለዋል። ገነነ በግላቸው የአዋሳ ዶሮ እርባታ ማዐከል ሥራ አስኪያጅ መሆናቸውን ገልጸው እንደ አንድ ዶሮ አርቢም ከፍተኛ የሆነ የዶሮ መኖ እጥረት መኖሩን ተናግረዋል።

በእነዚህ እና በሌሎችም ምክንያቶች ከፍተኛ የሆኑ ዶሮ አርቢዎች እንዲሁም ተደራጅተው ዶሮ የሚያረቡ ወጣቶች እና በግልም ዶሮ የሚያረቡ እና በቀን እስከ 100 ሺሕ እንቁላል ለገበያ የሚያቀርቡ ባለሀብቶች ከገበያ እየወጡ ነው። ባጠቃላይ የዶሮ እርባታ ሥራ ባለቤት የሌለው ተቋም ሆኗል በማለት ገልጸዋል።

አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው በከፍተኛ ደረጃ ዶሮ የሚያረቡ እና የእንሰሳት መኖ የሚያቀነባብሩ ግለሰብ የዘይት ፋብሪካዎች መዘጋት አንዱ ችግር መሆኑን ተናግረው ያሉትም ቢሆኑ ዘይት ከጨመቁ በኋላ የሚያገኙትን የፋጉሎ ተረፈ ምርት ወደ ውጭ አገራት ከሚልኩ ይልቅ አገር ውስጥ ላሉ የዶሮ እና የእንሰሳት አርቢዎች እንዲቀርብ መንግሥት ቢያመቻችልን ጥሩ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና አሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) ለዶሮ እና ለሌሎች እንሰሳት የመኖ አቅርቦት እጥረት መኖሩን እንደሚያውቁ ገልጸው በተለያዩ ስብሰባዎች ላይ ከዶሮ አርቢ ማሕበራት ጋር መነጋገራቸውን አሳውቀዋል። ችግሩ የተፈጠረው በተለያዩ ምክንያቶች እነደሆነ እና የመጀመሪያው ምክንያት ለእንሰሳት መኖ የሚሆኑ እንደ ፉርሽካ እና ፋጉሎ ያሉ የዘይት ተረፈ ምርቶች ላይ የሚጣለው ቫት አንዱ ነው ብለዋል።

ሌላኛው ለመኖ ማቀነባበሪያ ግብዓት ሚውለው ‘ፕሪሚስ’ ከውጭ አገር ስለሚመጣ አሁን ያለው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ዋጋው ከፍ እንዲል አድርጎታል ብለዋል። የዘይት ተረፈ ምርቶችን ወደ ውጭ አገራት መላክ መጀመራቸውም ሌላኛወ ተግዳሮት እነደሆነ አሳውቀዋል። እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ምርቱ ወደ ውጭ አገር ከሚላክ ይልቅ አገር ውስጥ የሚያስገኘው ጥቅም ታይቶ እንዳይላክ ማድረግ እንዲሁም፣ እንደ ረጅም ጊዜ መፍትሄ እነዚህ ዶሮ እና እንስሳት አርቢዎች ቆላማ አካባቢዎች ላይ እርሻዎች ኖሯቸው በቆሎም ሆነ አኩሪ አተር ቢያመርቱ የሚፈልጉትን የዶሮ መኖ ይሸፍናሉ ብለዋል።

ፍቅሩ(ዶ/ር) ችግሩን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትኩረት እንደሰጠው ገልጸው በእርሳቸው ተቋም ኀላፊነት ብቻ የማይፈታ መሆኑን አሰውቀዋል። ነገር ግን ውሳኔ በማይሰጡባቸው ተቋማት ሁሉ ውሳኔ ሰጭ አካል ባይሆኑም ችግሩ መኖሩን እያሳወቁ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 119 የካቲት 6 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here