ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ላይ ተወዳዳሪ አምራቾችን ካልፈጠረች የአገራት ሸቀጦች ማራገፊያ ልትሆን ትችላለች ተባለ

0
1024

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እንዳስታወቀው አገሪቱ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ተግባራዊ ከማድረጓ በፊት የንግዱ ማህረሰብን ብቁ ማድረግ ያስፈልጋል ብሏል
የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከፓን አፍሪካን ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ጋር በመተባበር የነፃ የንግድ ቀጠናው በሚኖረው ስጋትና ጠቀሜታ ዙሪያ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በአዲስ አበባ እየመከረ ነው።
በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ኢንጂነር መልዓኩ አዘዘው እንደገለፁት የአፍሪካን አህጉራዊ የንግድ ቀጠና ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት አምራች ድርጅቶችን ብቁና ተወዳዳሪ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
በኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ በርካታ ችግሮች ያሉበት በመሆኑ ለንግዱ ማህበረሰብ አትራፊ አይደለም ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ እነዚህ ችግሮች እስካልተፈቱ ድረስ የነፃ የንግድ ቀጠናው አዋጭ እንደማይሆን አንስተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በአገሪቱ ብቁ ነጋዴዎች ፣አለመኖር፣ የጥሬ እቃ አቅርቦት ችግር፣ ቴክኖሎጂ ክፍተት እና ጥራት ያለው ምርት አለመኖር ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት ጋር ተወዳዳሪ እንዳትሆን ያደርጋታል ብለዋል ኢንጂነር መልዓኩ።
የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና የገበያ አማራጮችን ከማስፋት አኳያ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ቢታወቅም ኢትዮጵያን የዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ የንግድ ማህረቡን ማንቃት ያስፈልጋልም ተብሏል ።
የኢትዮጵያ የንግድ ማህበረሰብ የተለያዩ ምርቶችን በአገር ውስጥ ከማምረት ይልቅ ከውጭ አገራት ማስገባትን ይመርጣሉ ፣ይህ ደግሞ አገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዲገጥመት ያደርጋል ። ኢትዮጵያ ከሰሞኑ ከዩክሬን እንቁላል ልታስገባ መሆኑም የችግሩ አንዱ ማሳያ ተደርጎ ተነስቷል። የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና በቅርቡ በይፋ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል ።


ቅጽ 2 ቁጥር 121 የካቲት 20 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here