የቪዛ ካርድ ክፍያን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት እየተሠራ ነው

0
710

በዓለም አቀፍ ደረጃ በክፍያ የቴክኖሎጂ መሪ የሆነው ቪዛ በኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያዎችን ለማስፋት በማሰብ ከሚመለከታቸው የፋይናንስ ሥነ-ምህዳር ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት በመስራት የዲጂታል ክፍያን ጥቅሞች ለሸማቾች ፣ ለነጋዴዎች ፣ ለገንዘብ እና ለመንግስት ተቋማት ለማስጠት ቁርጠኝነቱን አረጋግጧል ።
ኩባንያው ይህን ያስታወቀው ባለፈው ሐሙስ ባካሄደው የቪዛ ክፍያዎች መድረክ በአገሪቱ ውስጥ የዲጂታል ክፍያዎችን ለማዳበር በሚችሉ ዕድሎች ላይ ከዲጂታል ክፍያዎች ኢንዱስትሪ ተውካዮች በተወያየበት ወቅት ነው።
በመድረኩ ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለፈጠራቸው ሽርክናዎችን ይፋ ያደረገ ሲሆን ለአብነትም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በአህጉሪቱ ለሚገኙ የሼባ ማይልስ ካርድ በጋራ ጥቅም ላይ ለማዋል፣ ከአቢሲኒያ ባንክ እና ከ ዳሽን ባንክ ጋር ኦንላይን ግብይት ለመተግበር እና ለማሳድግ እንዲሁም የድንበር ተሻጋሪ ክፍያዎች ልማት ላይ ከምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ከሚሰራው እና ኤልክትሮኒክ ንግድን በማስፋፋት አገሪቱ የዲጂታል አቅሟን እንድትጠቀም ከሚሠራው ቤልካሽ ቴክኖሎጂስ ጋር ጥምረት ለመስራት ስምምነት መድረሱ ይጠቀሳል።
ከነዝህም በተጨማሪ ቪዛ ሀገር በቀል ይሆኑ የፍይናሺል ቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ለማሳደግ ብሎም የሥራ ፈጠራን ለማዳበር ቪዛ በሁሉም ቦታ የተሰኘ መረሃግብር በቅርቡ ይፋ አርጓል
“በአፍሪካ እጅግ አስደሳች ከሆኑት ሀገሮች በአንዷ ቪዛን ይዘን በመገኘታችን ደስታችን የላቀ ነው። በዚህ አጋጣሚም ከአጋሮቻችን ጋር በመሆን በገበያው የዲጂታል ግብይት ላይ ስንሰራ መቆየታችንን መግለጽ እወዳለሁ። ፋይናንሳዊ አካታችነት ቁልፍ ሚና በሚጫወትበት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ግቦችን የማሳካት ሂደት ውስጥ ተሳትፎ በማድረጋችንም ደስተኞች ነን። ብዙ ሰዎችን ወደ ፋይናንስ ስርዓቱ በማስገባት እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን በመደገፍ ረገድ የበኩላችንን ለማድረግ በቁርጠኝነት የተገኘን ሲሆን በዚህም ብዙ መልካም አጋጣሚዎች እንዳሉ አይተናል” ያሉት ሲኒየር ምክትል ፕሬዚዳንት እና በታችኛው አፍሪካ አገሮች የቪዛ ሀላፊዋ አይዳ ዲያራ ናቸው።”
የኢትዮጵያ መንግስት የዲጂታል ትራንስፈፎርሜሽንን ከግብ ለማድረስ በጁን 2020 በሀገሪቱ የመጀመሪያውን የዲጂታል ትራንስፈርሜሽን ስትራተጂ ይፋ ማደረጉን ተከትሎ የኤሌክትሮኒክ ግብይትን ጨምሮ ተከታታይ አዋጆች ወጥተዋል።
“ግብይትን ዲጂታል የማድረጉ ዕቅድ በተገቢ ክትትል ለኢትዮጵያዊያን በርካታ ጥቅሞችን ይሰጣልል። የተሻሻለ የዲጂታል መሠረተ ልማት ግለሰቦች እና ለአነስተኛ ንገድ ተቋማት የገንዘብ እንቅስቃሴያቸውን በፍጥነት፣ በትክክል፣ በተገቢውና በግልፀኝነት እንዲያከናውኑ ያስችላቸዋል። ግብይትን ዲጂታል ማድረግ በተጨማሪም ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገትን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ኢኮኖሚያዊ አካታችነትን ያቀላጥፋል” አይዳ ብለዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here