ተቀማጭነታቸዉን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሃገራት ዲፕሎማቶች፤ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በትግራይ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ መነጋገራቸዉ ተሰማ።
ከትናንት ከቀትር ጀምሮ እስከ ዛሬ ጠዋት ድርረስ ወደ መቀሌ የተጓዙት ተቀማጭነታቸዉን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሃገራት ዲፕሎማቶች፤ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለሥልጣናት ጋር ዛሬ ቀትር ላይ መቀሌ በሚገኝ ሆቴል ዉስጥ መወያየታቸዉ ታዉቋል። የዲፕሎማቶቹ ወደ መቀሌ መግባትን ተከትሎ ባንኮችን ጨምሮ በከተማዋ የሚገኙ ሱቆች የማኅበረሰብ መገልገያ ተቋማትን በመዝጋት የከተማዋ ነዋሪዎች ቤት በመቀመጥ አድማ መምታታቸዉ ተሰምቶአል።
አድማዉ በትግራይ ያለዉን አስከፊ ሁኔታ ለዲፕሎማቶቹ ለማሳየት ነዉ ሲሉ የከተማዋ ነዋሪዎች መናገራቸዉን የመቀሌዉ የጀርመን ድምጽ ዘግቧል፡፡
ቅጽ 2 ቁጥር 123 መጋቢት 3 2013



