ኮቪድ-19 በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ

0
795

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመሆኑ እና የስርጭት መጠኑም በአሳሳቢ ደረጃ እያሻቀበ በመምጣቱ ህብረተሰቡ መከላከያ ዘዴዎችን ሙሉ ለሙሉ እንዲተገብር የጤና ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ የፌደራል ፖሊስን ጨምሮ ከተለያዩ ተቋማት ጋር የኮቪድ-19 መከላከያ ዘዴዎችን ሙሉ ለሙሉ ማስተግበር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።
ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳሰፈሩት ፌደራል ፖሊስን ጨምሮ ከሰላም ሚኒስቴር፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፣ ከፌደራልና አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር ነው የተወያዩት።
ውይይቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የሚገኘውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በተመለከተ ከተጋረጠው ስጋት ለመውጣትና ህዝቡን ለመታደግ ያለመ ነው ብለዋል። በተለይም ደግሞ ከቅርብ ቀናት ወዲህ ቤዕለቱ በጤና ሚኒስቴር እና በሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አማካኝነት ወደ ሕዝብ በሚደርሰው የኮቪድ 19 ዕለታዊ መረጃ ላይ የቁጥሮች ማሻቀብ ኣሳቢ በመሆኑም አመላካች ናቸው። ለዚህ ደግሞ በሕብረተሰቡ ዘንድ ያለው መዘናጋት እና እንደቀደመው አለመጠንቀቅ ዋነኛ ምክንያት መሆኑንም በተደጋጋሚ የጤና ሚንስትሯ ሲናገሩ ይደመጣሉ። በአሁኑ ወቅት የኮቪድ 19 ክትባት ወደ አገር ውስጥ ግባቱን ተከትሎም የሕብረተሰቡ መዘናጋት እንደጨመረ እና በዛውም ልክ በቫይረሱ የሚጠቁት ሰዎች ቁጥርም መጨመሩ ተመላክቷል።


ቅጽ 2 ቁጥር 124 መጋቢት 11 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here