ብሔራዊ ምበርጫ ቦርድ የዕጩዎች የምዝገባና አጠቃላይ የኦፕሬሽን ሂደቶችን በተመለከተ መጋቢት 8 / 2013 የዕጩዎች የምክክር መድረክ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር አካሄዷል።
በእለቱም የምርጫው ግልጽነትና ፍትሐዊነትን ለመጨመር ያስችል ዘንድ በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የሚኖረውን የዕጩዎች ቅደም ተከተል በሎተሪ ዕጣ እንደሚወሠንም አክለው ገልጸዋል።
በዕጩዎች ምዝገባ ወቅት ለሚኖሩ አቤቱታዎች በአጭር ጽሑፍ መልዕክትና በስልክ እንዲሁም ፓርቲዎቹ ይቀሉናል ባሏቸው አማራጮች ሁሉ በመጠቀም መፍትሔ እንዲያገኙ እንደመመቻቸቱ መጠን፤ የዕጩዎች ምዝገባ መጠናቀቁን ተከትሎ የሚቀርቡትን አቤቱታዎች ለማስተናገድ ቦርዱ እንደሚቸግር ተገልጿል።
ያም ሆኖ ግን በበቂ መረጃ ተደግፈው በክትትል ላይ ያሉ ጉዳዮችን እንደሚመልስና የዕጩዎች ምዝገባም ፍጽም ዝግ ነው ማለት እንዳልሆነ ግን ተብራርቷል።
ቅጽ 2 ቁጥር 124 መጋቢት 11 2013



