የእጩ ምዝገባን መጠናቀቅ ተከትሎ ለፖለቲካ ፓርቲዎች በሚሰጠው የአየር ሰዓት ድልድል ሂደት ላይ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ውይይት አደረጉ።
በውይይቱ ላይ ባለስልጣኑ ለአየር ሰዓትና የጋዜጣ አምድ ድልድሉ ያከናወናቸውን መሰረታዊ የአውቶሜሽን ስራዎችን እንዲሁም የቀሩ ሂደቶችን ለቦርዱ አቅርቧል።
ለአየር ሰዓትና ለጋዜጣ አምድ ድልድሉ የተዘጋጀውን የእጣ ማውጫ ሶፍትዌር እንደተዘጋጀ እና መሰረታዊ ግብዓቶች ተሟልተው እንደቀረቡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስራውን እንደሚያጠናቅ እና የአየር ሰዓት እጣ አወጣጥ ስርዓቱንም የቦርዱ አመራሮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመገናኛ ብዙሃንና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እንደሚያከናወን ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡
ቅጽ 3 ቁጥር 125 መጋቢት 18 2013



