ምርጫ በማድረግ ኢትዮጵያ ትድናለች ማለት ችግሮቿን ማሳነስ ሊሆን እንደሚችል ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለፁ

0
763

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መሪ ፕሮፌሰር ብርሃ ነጋ ከአሐዱ ቴሌቪዥን ኬላ ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት አገሪቱ የገጠማት ችግሮች ሁሉ በምርጫ ይፈታሉ ማለት አይቻልም ብለዋል። ይህን ማለት ችግሮቹን ማሳነስ ይሆናል ያሉት ፕሮፌሰሩ ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ያሉባት ሀገር ነች አብዛኛው ማህበረሰብ ድሆች ናቸው ብለዋል።
አገሪቷ ከፍተኛ የሆነ የምጣኔ ሀብት እና የማህበራዊ ችግሮች አሉባት፣ እነዚህን መሰረታዊ የሆኑ ችግሮችን መፍታት ሲቻል ኢትዮጵያ ማዳን እንደሚቻል ገልፀዋል። ይህን ለመፍታት ረዥም ጊዜ ይወስዳል ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ምርጫ ማካሄድ እነዚህን ሁሉ ችግሮች በአንድ ጀምበር እንደማይፈታ መታወቅ አለበት ብለዋል።
የምጣኔ ሀብቱም ሆነ የማኅበራዊ ችግሮች መሰረቱ የተፈጠረው የፖለቲካ ስርዓቱ ችግሮቹን በተረጋጋ እና ዘላቂ በሆነ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ስርዓት ባለመዘርጋቱ እንደሆነ ተናግረዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 126 መጋቢት 25 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here