አዋሽ ባንክ ልዩ ትኩረት ለሚሹ 17.9 ሚሊየን ብር መለገሱን ተናገረ

0
1417

ባንኩ ዛሬ በእሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ባዘጋጀው የድጋፍ መርሐ-ግብር ላይ ለ6 ልዩ ትኩረት ለሚሹ ድርጅቶችና ተቋማት የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ይፋ አድርጓል። የአዋሽ ባንክ እ.ኤ.አ ለ2019/20 የሂሳብ ዓመት ከመደበው ብር 17.9 ሚሊዮን የገንዘብ ልገሳ መርሐ-ግብር ተጠቃሚ ለመሆን በርካታ ተቋማት ጥያቄ ማቅረባቸውን አሳውቋል። ማመልከቻቸውንና የፕሮጀክት ፕሮፖዛላቸውን በመቀበል ተገቢውን መስፈርት አሟልተው ለተገኙ ተቋማት ከአድሎአዊ አሰራር ነፃ በሆነ መልኩ እና ለህብረተሰቡ ሊያበረክቱ ከሚችሉት አገልግሎት አንፃር መዝኖ ለኢትዮጵያ ማየትና መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማህበር 700,000.00 ብር ፤ ለዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ፋውንዴሽን1,200,000.00 ብር፤ ለኤስ ኤን ቪ ኔዘርላንድስ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን 2,000,000.00 ብር ፤ ለኬር ኢትዮጵያ 2,000,000.00 ብር ፤ ለሴንትሮ አሉቶ ፐር ኢትዮጵያ 2,000,000.00 ብር እንዲሁም ለዲቦራ ፋውንዴሽን 10,000,000.00 ብር ድጋፍ ማድረጉን ይፋ አድርጓል። የተከፈለ የካፒታል መጠኑ 8.1 ቢሊዮን ብር መድረሱን የሚናገረው አዋሽ ባንክ፣ ላለፉት 26 ዓመታት የልማት፣ የሰብዓዊ ዕርዳታና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ ከማድረጉ በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ስራዎችንም ሲያከናውን መቆየቱን ተናግሯል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here