አዋሽ ባንክ ልዩ ትኩረት ለሚሹ ድርጅቶችና ተቋማት 17.9 ሚሊዮን ብር መለገሱን ተናገረ

0
622

አዋሽ ባንክ ባዘጋጀው የድጋፍ መርሃ-ግብር ላይ ለ6 ልዩ ትኩረት ለሚሹ ድርጅቶችና ተቋማት 17.9 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ይፋ አድርጓል።
የአዋሽ ባንክ እ.አ.አ ለ2019/20 የሂሳብ ዓመት ከመደበው ብር 17.9 ሚሊዮን የገንዘብ ልገሳ መርሃ-ግብር ተጠቃሚ ለመሆን በርካታ ተቋማት ጥያቄ ማቅረባቸውን አሳታውቋል። ማመልከቻቸውንና የፕሮጀክት ፕሮፖዛላቸውን በመቀበል ተገቢውን መስፈርት አሟልተው ለተገኙ ተቋማት ከአድሎአዊ አሰራር ነጻ በሆነ መልኩ እና ለሕብረተሰቡ ሊያበረክቱ ከሚችሉት አገልግሎት አንፃር መዝኖ ለኢትዮጵያ ማየትና መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኃበር 700,000.00 ብር ፣ ለዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ፋውንዴሽን 1,200,000.00 ብር፤ ለኤስ ኤን ቪ ኔዘርላንድስ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን 2,000,000.00 ብር ፤ ለኬር ኢትዮጵያ 2,000,000.00 ብር ፤ ለሴንትሮ አሉቶ ፐር ኢትዮጵያ 2,000,000.00 ብር እንዲሁም ለዲቦራ ፋውንዴሽን 10,000,000.00 ብር ድጋፍ ማድረጉን ይፋ አድርጓል።
የተከፈለ የካፒታል መጠኑ 8.1 ቢሊዮን ብር መድረሱን የሚናገረው አዋሽ ባንክ፣ ላለፉት 26 ዓመታት የልማት፣ የሰብዓዊ ዕርዳታና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ ከማድረጉ በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ስራዎችንም ሲያከናውን መቆየቱን ተናግሯል።


ቅጽ 3 ቁጥር 133 ግንቦት 14 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here