‹‹የብሔራዊ ክብር በኅብር›› ግብረ ኃይል ለእንግሊዝ ኤምባሲ መልእክት አደረሰ

0
837

የብሔራዊ ክብር በኅብር ግብረ ኃይል ለእንግሊዝ ኤምባሲ ባደረሰው መልእክት ኢትዮጵያ እየገነባች ያለችውን ታላቁ የሕዳሴ ግድብ አስፈላጊነት ገልጿል፡፡ የአገሪቱን የምርጫ ፍላጎት እና ሉዓላዊነት እንዲያከብሩ፣ በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገቡም ጠይቋል፡፡
ግብረ ኃይሉ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት መደገፍ እንደሚገባ በመልዕክቱ አስተላልፏል፡፡
የግብረ ኃይሉ የተቃውሞ እንቅስቃሴ “ከአገራችን ላይ እጃችሁን አንሱ” የሚል መሪ ሃሳብ ያነገበ ነው፡፡ ለአሜሪካ ኤምባሲ እና ለአዉሮፓ ኅብረት በተለያዩ የመረጃ ማስተላለፊያ መንገዶች አማካይነት መልዕክቱ እንዲደርስ መደረጉ ተገልጿል፡፡
በኤምባሲው ከእንግሊዝ የፖለቲካ ቃል አቀባይ እና ካዉንስል ጋር የአንድ ሰዓት ውይይት ተደርጓል ተብሏል፡፡ በዚህም ግብረ ኃይሉ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ትክክለኛ መረጃ ለመስጠት ጥረት ማድረጉ ተጠቅሷል፡፡ መልዕክቱ ለእንግሊዝ መንግሥት እንደሚደርስም ቃል ተገብቷል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነቱን ማጠንከርና ለአገር ሉዓላዊነት መከበር ከእኔነት ይልቅ እኛነትን መምረጥ ትልቁ መፍትሔ መሆኑንም የብሔራዊ ክብር በኅብር ግብረ ኃይል መልእክት አስተላልፏል።


ቅጽ 3 ቁጥር 134 ግንቦት 21 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here