ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ኃላፊነት የማይሰማቸው የሚዲያ ተቋማት እና ራሳቸውን የማኀበረሰብ “አንቂ” ብለው የሰየሙ ግለሰቦች በቦርዱ በሕጋዊነት የተመዘገቡ የአገር አቀፍ እና የክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ የሚያደርጉትን መሰረተ ቢስ የሥም ማጥፋት ዘመቻ ለማስቆም ቦርዱ ሕጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባ ጠይቋል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች መዝጋቢ እና ተቆጣጣሪ የሆነው ምርጫ ቦርድ ሕገ መንግስቱን እና ሌሎች የአገሪቱ ሕጎች ማሟላታቸውን አረጋግጦ የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የሰጣቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ኃላፊነት በማይሰማቸው አካላት ሕጋዊነታቸውን የሚሸራርፍ መሰረተ ቢስ ውንጀላ ሲፈፀምባቸው ቦርዱ ጠንካራ የእርምት እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባ ነእፓ አሳስቧል፡፡ ባላፉት ጊዜያት ኃላፊነት በማይሰማቸው አካላት ዒላማ ከተደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ ነእፓ መሆኑ ፓርቲው ጠቁሟል፡፡
ቅጽ 3 ቁጥር 134 ግንቦት 21 2013



