ኢሠማኮ አንድ ሺሕ 252 የምርጫ ታዛቢዎችን እንደሚመድብ አስታወቀ

0
1340

የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አንድ ሺሕ 252 የምርጫ ታዛቢዎችን በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች እንደሚልክ አስታውቋል። ኮንፌዴሬሽኑ ‹ሶሊዳሪቲ ሴንተር› ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን የሦስት ቀናት የታዛቢዎች ሥልጠና ማጠናቀቁን ጠቁሟል፡፡ ኢሠማኮ ምርጫውን ለመታዘብ በርካታ ዝግጅቶችን ማድረጉን እና ከእነዚህም መካከል የመራጮች ትምህርት በስፋት መስጠቱን ይፋ አድርጓል።
የኢሠማኮ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ኮንፌዴሬሽኑ ለስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ከአምስት ሺሕ 500 በላይ የምርጫ ታዛቢዎችን የመላክ እቅድ እንደነበረው ተናግረው፣ በአቅም ማነስ ምክንያት ዕቅዱን ማሳካት እንዳልቻለ ጠቁመዋል፡፡ ከተለያዩ የሙያ ማህበራት ተወክለው በሥልጠናው የተሳተፉ ሠራተኞች በበኩላቸው ከስልጠናው ጥሩ ግንዛቤ ማግኘታቸውንና ለአገራዊ ምርጫው ስኬት የድርሻቸውን ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸው ተገልጿል፡፡


ቅጽ 3 ቁጥር 135 ግንቦት 28 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here