ግብፅ ሁለተኛውን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ኢትዮጵያ መጀመሯን አስታወቀች

0
1039

የግብፅ  የመስኖ ሚኒስትር ሁለተኛው ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት መጀመሩን ኢትዮጵያ ይፋ ማድረጓን በትናንትናው እለት አስታወቁ፡፡

የመስኖ ሚኒስትሩ ሞሃመድ አብደል-አቲ ግብፅ ለቀጠናው መረጋጋት ሥጋት ነው የምትለውን ይህ እርምጃ ውድቅ እንደምታደርግም በመግለጫቸው ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በብሉ ናይል ላይ ያለው ግድብ ለኢኮኖሚ እድገቷ እና ለህዝቧ በቂ ኃይልን ለመስጠት ወሳኝ ነው እንደሆነ ታምናለች፡፡

ግብፅ ግድቡ ከናይል የምታገኘው የውሃ አቅርቦት ላይ በሚያመጣው ጫና ምክንያት እንደ ከባድ ስጋት ትመለከተዋለች ሲሉም ሚኒስቴሩ በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡

ሌላኛዋ የናይል ወንዝ ተፋሰስ ሀገር የሆነችው ሱዳን በበኩሏ በግድቡ ደህንነት እና በራሷ ግድቦች እና የውሃ ጣቢያዎች ላይ ስለሚያስከትለው ጉዳት ስጋቷን ገልፃለች፡፡

የተጠራቀመው የውሃ መጠን የሚወሰነው በኢትዮጵያ ውስጥ በሚዘንበው ወቅታዊ ዝናብ መጠን ላይ መሆኑን የግብፅ መስኖ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሙሃመድ ጋሀኒም ለአካባቢው የቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል፡፡

“በአባይ ላይ አሁን ምንም አይነት ውጤት አናገኝም፤ ከፊታችን አንድ ወር ወይም አንድ ወር ተኩል ይኖረናል” ብለዋል ቃል አቀባዩ፡፡

በግድቡ ሥራ ላይ ግብፅና ሱዳን በሕጋዊ መንገድ አስገዳጅ የሆነ ስምምነት ለማድረግ ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ ያካሄዱ ቢሆንም ድርድሩ በተደጋጋሚ ቆሟል፡፡

ዲፕሎማሲያዊው ግፊት ባለፈው የበጋ ወቅት የመጀመሪያውን ግድብ ከመሙላቱ በፊት እና በቅርብ ሳምንታትም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም / ቤት ሐሙስ በጉዳዩ ላይ ይወያያል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን አብደል አቲ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ለማሳወቅ ለምክር ቤቱ ደብዳቤ መጻፉን በመግለጫቸው አመልክተዋል ሲል የሮይተርስ ዘገባ አመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያ በመጨረሻ በአጎራባች አገሮች ቁጥጥር ስር በነበረው የአባይ ውሃ ላይ መብቴን እየተጠቀምኩ ነው ስትል ማስታወቋም አይዘነጋም ፡፡

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here