የግብርናውን ዘርፍ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ምርታማነትን ማሳደግና ለማምረቻው ዘርፍ ግብዓት እንዲሆን ማድረግ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

0
291

የግብርናውን ዘርፍ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ምርታማነትን ማሳደግና ለማምረቻው ዘርፍ ግብዓት እንዲሆን ማድረግ ላይ መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

ኢትዮጵያ የግብርና ዘርፏን ለማዘመንና የግብርና ምርቶች ላይ እሴት በመጨመር ከዘርፉ የምታገኘውን ገቢ ለማሳደግ እየሰራች ትገኛለች፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሐመድ (ፒ ኤች ዲ) የግብርናውን ዘርፍ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ምርታማነትን ማሳደግና ለማምረቻው ዘርፍ ግብዓት እንዲሆን ማድረግ ላይ መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የግብርናውን ዘርፍ በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በሚደረገው ጥረት የዘርፉ ባለሙያዎች ትብብር ወሳኝ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የአርሶ አደሩን ህይወት ለማሻሻልና ግብርናው እንዲዘምን ለማድረግ የዲጂታል ግብርና ፕላትፎርም መገንባትና የግብርና ቴክኖሎጂ ስራ ፈጠራ ላይ የተሰማሩትን መደገፍ እና ማበረታታት ላይ ይሰራል ብለዋል፡፡

የ‹‹ለርሻ›› መስራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ አብረሃም እንድሪስ ለአርሶ አደሮች በአጭር የስልክ ቁጥር ጥሪ የግብርና መረጃዎችን በተለያዩ የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች እየሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በውይይቱም ኢትዮጵያ ያሏትን በርካታ የግብርና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን አቅም በመጠቀም የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፋት ላይ መስራት እንደሚገባም መጠቆሙም ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች የግርናውን ዘርፍ ለማዘመን፣ የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማሳደግና መረጃ እንዲያገኙ ለማድረግ ሰለሚሰጧቸው አገልግሎት፣ በዘርፉ ስላሉ ተግዳሮቶችና መፍትሄዎች ላይ ውይይት ማካሄዳቸውም ታውቋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here