ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 196 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው ተመለሱ

0
791

ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 196 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎቻችንን በስፋት ለመመለስ በታያዘው እቅድ መሰረት በርካታ ዜጎቻችን በየቀኑ ወደ አገራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።

በትናንትናው ዕለትም 196 ሴቶችና 88 ህጻናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 2 ሺህ 196 ተመላሾች ወደ አገራቸው ገብተዋል።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ተገቢው አቀባበል እንደተደረገላቸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here