በሐምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ፤ ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ ያሉ ሌሎች ምርቶች በሰኔ ወር የመሸጫ ዋጋ እንደሚቀጥሉ መወሰኑን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በላከው መግለጫ በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ ያለው ነባራዊ የነዳጅ ምርት መሸጫ ዋጋ በየወሩ በመጨመር ላይ የሚገኝ ሲሆን በዚሁ መሰረት የችርቻሮ መሸጫ ዋጋው ቢሰላ የተለየ ይዘት እንደሚኖረው አመልክቷል።
ነገር ግን መንግስት የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት ኢኮኖሚያዊ እና ማሕበራዊ እንቅስቃሴው ተረጋግቶ እንዲቀጥል የሐምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ባለፈው ወር በነበረበት እንዲቀጥል ወስኗል።
የአውሮፕላን ነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን በሚመለከት የዓለም ነዳጅ ዋጋ መሰረት በማድረግ አዲስ አበባ ላይ በሊትር ሲሸጥበት ከነበረው 48 ብር 22 ሳንቲም ወደ 51 ብር ከ76 ሳንቲም ከፍ እንዲል መወሰኑን በመግለጫው አስታውቋል።



