ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 212 ዜጎች ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎች ወደ አገራቸው በስፋት ለመመለስ በተያዘው እቅድ መሰረት በርካታ ዜጎቻችን በየቀኑ ወደ አገራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።
በትናንትናው ዕለትም 381 ሴቶችና 183 ህጻናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 2 ሺህ 212 ዜጎች ወደ አገራቸው ገብተዋል።
ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል እንደተደረገላቸው ከቃል አቀባይ ጽህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።






