ብልጽግና ካሸነፈ በምርጫው የተሳተፉ ፓርቲዎችን በመንግሥት መዋቅር እንደሚያሳትፍ ገለጸ

0
473

ብልፅግና ፓርቲ በምርጫው የሚያሸንፍ ከሆነ በምርጫው የተፎካከሩ ፓርቲዎችን በየደረጃው ባለው የመንግሥት መዋቅር የሚያሳትፍ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
የሲቪክ ማኅበራት ደርጅቶች ምክር ቤት በዘንድሮው ምርጫ ለተፎካከሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምስጋና መርሃ ግብር አካሂዷል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዐቢይ በምርጫው ፓርቲያቸው አሸናፊ ከሆነ ተፎካካሪ የነበሩ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ከታች ጀምሮ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ እንደሚሳትፉ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ዘንደሮ ነጻና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማካሄድ የቻለችው ሁላችንም ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ በመሥራታችን ነው ሲሉም ተናግረዋል።
በምርጫው ዕለት ዜጎች ኢትዮጵያ አሸናፊ እንድትሆን ወጥተው ድምፅ በመስጠታቸውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ኢትዮጵያዊያን ከፖለቲካ ይልቅ አገር ትቀድማለች የሚል መርህ አንግበው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማካሄድ አገራቸውን አሸናፊ አድርገዋልም ነው ያሉት። የሲቪክ ማኅበራት ደርጅቶች ምክር ቤት በምርጫው ለተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባዘጋጀው የምስጋና ምሽት የኃይማኖት አባቶች፣ ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 140 ሐምሌ 4 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here