የአፋር ክልል ተፎካካሪ ፓርቲዎች ምርጫ እንዲደገም ወይም ሌላ መፍትሔ እንዲሰጥ ጠየቁ

0
287

የአፋር ክልል ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በአፋር ክልል ሰኔ 14/2013 የተደረገው ምርጫ ፍትሐዊ፣ ተአማኒ እና ዴሞክራሲያዊ ባለመሆኑ ምርጫው እንዲደገም ጠይቀዋል። የፓርቲዎቹ የጋራ ምክር ቤት ምርጫው ድጋሚ የማይደረግ ከሆነ፣ ሌላ የፖለቲካ መፍትሔ በአስቸኳይ መፈለግ አለበት ብሏል።
የአፋር ክልል ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል የሆኑት ፖለቲካ ፓርቲዎች የአፋር ነፃ አውጪ ግንባር፣ የአፋር ሕዝብ ፓርቲ፣ የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር እና የአፋር ሕዝብ ፍትሕ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሲሆኑ፣ ፓርቲዎቹ በክልሉ የተደረገው ምርጫ ከፍተኛ ችግር የተስተዋለበት በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብለዋል። ፓርቲዎቹ እንደሚሉት ከሆነ ምርጫው በአፋር ክልል ገና ከጅምሩ የመራጮች ካርድ ያለ አግባብ በግለሰቦች እጅ የገባበት ሁኔታ ነበር ብለዋል።
በክልሉ በምርጫው ከታዩ ችግሮች መካከል ታዛቢዎችን ከምርጫ ጣቢያ ማባረር፣ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አለመኖር፣ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት እንዲመርጡ ማድረግ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ገለልተኛ አለመሆን፣ ያልታወቁ ምርጫ ጣቢያዎች መክፈትና የተሳሳቱ የድምጽ መስጫ ወረቀቶችን በማቅረብ መራጮችን ማደናገር የሚሉት ይገኙበታል ብለዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 140 ሐምሌ 4 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here