ኢትዮጵያ ያካሄደችው ምርጫ የተቺዎችን አፍ ያዘጋ ነው ሲሉ አንድ የምስራቅ አፍሪካ የፖለቲካ ተንታኝ አስታወቁ

0
592

ኢትዮጵያ ያካሄደችው ምርጫ ውጤታማ መሆኑ፣ ከተለያዩ ወገኖች ሲሰነዘሩ የነበሩት ትችቶችን በሙሉ ውድቅ ያደረገ ነው ሲሉ የምስራቅ አፍሪካ ኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት ላውረንስ ፈሪማን ተናገሩ።
ፊሪማን ኢትዮጵያዊያን ያካሄዱት 6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ምን ያህል ለዲሞክራሲ መጎልበት ፍላጎት እንዳላቸው ያሳዩበት ነበረም ብለዋል።
ምዕራባውያን ሚዲያዎች እና መንግሥታት በኢትዮጵያ ላይ የነበራቸው የተዛባ አመለካከት የቀየረ ከመሆኑም ባሻገር የአገሪቱን የዲሞክራሲ ሂደት የጠቆመ ነው ብለዋል።
ላውረንስ ፈሪማን በትንታኔያቸው እንደ ማሳያ የተጠቀሙት የአፍሪካ ኅብረት የታዛቢዎች ቡድን ያወጣውን መረጃ ነው።
የኅብረቱ ታዛቢ ቡድን ምርጫው አንዳንድ እጥረቶች የነበረበት ቢሆንም፣ እጅግ ሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ ሂደቱ የጠበቀ እንደነበረ አስታውቋል ያሉት ተንታኙ፣ ይህም በምዕራባውያን ዘንድ ተቀባይነት ያላገኝ ጉዳይ እንደሆነም ነው ላውረንስ የተናገሩት።
አሜሪካ እንዲሁም የአውሮፓ አገራት ኢትዮጵያን ማመስገን እና እንኳን ደስ አለሽ ሊሉ ይገባ ነበር፣ ሆኖም ዝምታ ነው የመረጡት፣ ይህ የምርጫው ውጤታማነት የሚገልጽ ነው ሲሉ ነው ሐሳባቸውን የገለጹት።
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ላከናወነው ትልቅ ተግባር የውጭ አገራት ምስጋና ማቅረብ የነበረባቸው ቢሆንም፣ ወጪት ሰባሪነታቸውን በግልጽ አሳይተዋል እናም በአገሪቱ የፈጠሩት ችግር ሁሉ የሐሰት መሆኑ ሊገባቸው ይገባል ብለዋል ላውረንስ ከምርጫው በፊት እና ከምርጫው በኋላ ስለ ኢትዮጵያ የውሸት ዜናቸውን ሲያሰራጩ የከረሙት የምዕራባውን ሚዲያዎች አሁን በሌላ የውሸት አጀንዳ ተጠምደዋል ይህ የሚያሳየው ደግሞ የአገሪቱ ጠላት መሆናቸውን ነው ብለዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 140 ሐምሌ 4 2013 ፍሪማን።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here