በአንድ ጀምበር 281 ሚሊዮን 107 ሺህ 223 ችግኞችን የመትከል የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በኦሮሚያ ክልል በይፋ ተጀምሯል።
ከዕቅዱ ውስጥም እስከ ጠዋቱ 3 ሰዓት ድረስ ከ70 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን የኦሮሚያ ግብርና እና የተፈጥሮ ሀብት ቢሮ አስታውቋል።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብሩ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሚገኙ 19 ከተሞች እና 21 ዞኖች ውስጥ እየተከናወነ እንደሚገኝም ኦቢኤን ዘግቧል።
የመርሐ-ግብሩ ዕቅድ ሙሉ ለሙሉ ከተከናወነ ክልሉ በአንድ ቀን 281 ሚሊዮን 107 ሺህ 223 ችግኞችን በመትከል ሪከርድ እንደሚይዝ ታውቋል።






