የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በጣት አሻራ እና የትራፊክ አደጋ ምርመራ ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች አስመረቀ

0
911

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ ከክልሎች እና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ በጣት አሻራ እና የትራፊክ አደጋ ምርመራ ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው በጣት አሻራ ምርመራ አርባ ስድስት ሰልጣኞን ለ6 ወር እና በትራፊክ አደጋ ምርመራ አርባ ሰልጣኞችን ለ3 ወር በማሰልጠን በአጠቃላይ ሰማንያ ስድስት ሰልጣኞችን ሀምሌ 3/2013 ዓ.ም አስመርቋል፡፡

በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ ሪፖርት ያቀረቡት በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የአጫጭር ልዩ ልዩ ፖሊስ ኦፕሬሽን ስልጠና ዲፓርትመንት ሀላፊ ኢ/ር እናት መንግስቱ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የሀገራችንን የፖሊስ ሙያ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የዕውቀት፣ የክህሎት እና የአመለካከት ለውጥ የሚያመጣ የፖሊስ አመራርና ባለሙያ ለማፍራት በተለያዩ ረጃጅም እና አጫጭር የአቅም ግንባታ እና የሙያ ማሻሻያ ስልጠናዎችን በመስጠት የዘመነ የፖሊስ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ ከፍተኛ የሆነ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የአጫጭር ልዩልዩ ፖሊስ ኦፕሬሽን ስልጠና ዳይሬክተር ኮ/ር ካሳሁን ገ/ዮሐንስ እንደገለፁት የወሰዳችሁት የጣት አሻራ እና የትራፊክ አደጋ ምርመራ ትምህርት ሀገራችን የነበረባትን የባለሙያ እጥረት የሚቀንስ እና ሳይንሳዊ የወንጀል ምርመራ ዘዴን የሚያስፋፋ በመሆኑ በስልጠና ቆያታችሁ ያገኛችሁትን ዕውቀት እና ክህሎት ወደ ተግባር በመለወጥ ህዝባዊ ወገተኝነታችሁን በፍፁም ታማኝነት እንድትወጡ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ተመራቂ ሰልጣኞቹ በበኩላቸው በአጭር ጊዜ ከፍተኛ የሆነ ትምህርትና ስልጠና ከዩኒቨርሲቲው ማግኘታቸውን ገልፀው በስልጠና ቆይታቸው የዩኒቨርሲቲው መምህራኖች ፣አሰልጣኞች እና የአካባቢው ማህበረሰብ ላደረጉላቸው አስተዋፅኦ ምስጋና ማቅረባቸውን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ማህበራዊ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here