ሁለተኛው ዙር የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት ከነገ ጀምሮ በጤና ተቋማት ይሰጣል

0
646

ሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ከነገ ጀምሮ በጤና ተቋማት እንደሚሰጥ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን የኮቪድ ክትባት ከወሰዱ ሶስት ወር የሞላቸው ዜጎች ከነገ ጀምሮ እንደሚከተቡ እና በክልሎች ደግሞ ክትባቱን ከሐምሌ 9 ጀምሮ መውሰድ እንደሚቻል ሚኒስትሯ ገልፀዋል።

ክትባቱን ተደራሽ ለማድረግ መንግሥት ከአጋር አካላት ጋር እየሰራ ነው ያሉት ዶ/ር ሊያ 400 ሺህ የአስትራዜኒካ ክትባት ለሁሉም ክልሎች እየተሰራጨ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በቀጣይም 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ክትባት ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባ የጠቀሱት ሚኒስትሯ የትራንስፖርት ዘርፍ ሰራተኞች፣ ፖሊሶች፣ መምህራን፣ የባንክና የፍርድ ቤት ሰራተኞች፣ ተጓዳኝ የጤና ችግር ያለባቸው እና በእድሜ የገፉ ዜጎች እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን ሰራተኞች የመጀመሪያውን ዙር ክትባት እንዲወስዱ ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል።

አዲሱ የኮቪድ ዝርያ ዴልታ በኢትዮጵያ ስለመከሰቱ ጥናት እየተደረገ እንዳለም ሚኒስትሯ በመግለጫቸው አንስተዋል።

እስካሁን ከ277 ሺህ በላይ ዜጎች ኮቪድ-19 ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን 4343 በኮቪድ-19 ለሞት መዳረጋቸውም ታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here