የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ2014 በጀት ዓመት 70 ቢሊዮን 670 ሚሊዮን ብር በጀት ወሰነ

0
909

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ2014 በጀት ዓመት 70 ቢሊዮን 670 ሚሊዮን ብር በጀት መወሰኑን የአስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬተሪያል ቢሮ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ በ2014 በጀት ዓመት ለካፒታል እና መደበኛ ስራዎች፤ የከተማዋን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስቀጠል እና የነዋሪዎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ለማስቻል በአጠቃላይ 70 ቢሊዮን 670 ሚሊዮን 216 ሺህ 028.31 ብር በጀት በመወሰን ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መርቷል፡፡

የ2014 በጀት ድልድል በ2013 በጀት ዓመት ከተያዘው በጀት ጋር ሲነጻጸር በ9 ቢሊዮን 319 ሚሊዮን 594 ሺህ 613.31 ብር ወይም የአስራ አምስት ነጥብ አስራ ዘጠኝ በመቶ ዕድገት አለው ተብሏል፡፡

ከተማ አስተዳዳሩ የቀጣይ 10 ዓመት እና 5 ዓመት መሪ ዕቅድን የተመለከቱ የትኩረት አቅጣጫዎችንና ስትራቴጂክ ግቦችን መሰረት ባደረገ መልኩ በ2014 በጀት ዓመት ለኮንስትራክሽን ዘርፍ፤ ለውሃና ፍሳሽ ዘርፍ፤ ለመንገድ ልማት ዘርፍ፤ ለትምህርትና ስልጠና ዘርፍ፤ ለትራንስፖርት ዘርፍ፤ የአረንጓዴ ልማት ዘርፍ፤ ጤና ዘርፍ እና ለቤቶች ልማት ዘርፎች ከፍተኛ በጀት መመደቡን አስታውቋል፡፡

በከተማ ደረጃ ለሚገኙ የማዕከል መስሪያ ቤቶች በጠቅላላው 46 ቢሊዮን 559 ሚሊዮን 320 ሺህ 315.98 ብር የተመደበ ሲሆን ከአጠቃላይ በጀት ውስጥ ስልሳ አምስት ነጥብ ሰማንያ ስምንት በመቶ ድርሻ እንዳለው ተገልጿል፡፡

ለማዕከል መ/ቤቶች ከተመደበው በጀት ውስጥ ለመደበኛ ብር 16 ቢሊዮን 248 ሚሊዮን 362 ሺህ 343.73 ሀያ ሁለት ነጥብ ዘጠና ዘጠኝ በመቶ እና ለካፒታል ብር 30 ቢሊዮን 310 ሚሊዮን 957 ሺህ 972.25 አርባ ሁለት ነጥብ ሰማንያ ዘጠኝ በመቶ ተደልድሏል።

ለክፍለ ከተሞች የተመደበ በጀት ደግሞ 24 ቢሊዮን 110 ሚሊዮን 895 ሺህ 712.33 ብር ከአጠቃላይ በጀት ሰላሳ አራት ነጥብ አስራ ሁለት በመቶ ድርሻ እንዳለው ተገልጿል፡፡

ከዚህ ውስጥ ለመደበኛ በጀት ብር 20 ቢሊዮን, 541 ሚሊዮን 879 ሺህ 040.39 ብር ወይንም ሀያ ዘጠኝ ነጥብ ሰባት በመቶ እና ለካፒታል ደግሞ 3 ቢሊዮን 569 ሚሊዮን 016 ሺህ 671.94 ብር ወይንም አምስት ነጥብ ዜሮ አምስት በመቶ በመሆን መደልደሉም ታውቋል።

በጀቱን ታክስ ከሆኑና ካልሆኑ፤ ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች፤ ከሌሎች ምንጮች ማለትም ከብድርና ከዕርዳታ እንዲሁም ካለፈው በጀት ዓመታት ተራፊ ካሽ በጀቱን ለሟሟላት በእቅድ መያዙም ታውቋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here